ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮች ጋር ተወያዩ

159
መስከረም 7/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮችና ከኢትዮጵያ እስልምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ። የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተወካዮችና የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ውይይት የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞቻቸው ጋር ያላቸውን አብሮነት ለመግለጽ ከመስቀል  በዓል በፊት በሚደረግ የጽዳት ሥራ ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸውላቸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተደረገው ውይይት ከመስቀል በዓል በፊት በሚደረግ ጽዳት ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል። በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስን ጨምሮ ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ተገኝተዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም