ሴኔጋል የጡትና የማህፀን ጫፍ ካንሰር ለታመሙ ሴቶች ነጻ ህክምና ልትጀምር ነው

64
  ኢዜአ፤ መስከረም 7/2012 የሴኔጋል መንግሥት በጡት እና የማህፀን ጫፍ ካንሰር ህመም ለሚሰቃዩ ሴቶች ከመጪው ጥቅምት ወር ጀምሮ በነጻ የኬሞቴራፒ ህክምና እንደሚሰጥ አስታውቋል። በሀገሪቱ የፀረ ካንሰር ሊግ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፋትማ ጉኤኖን እንዳሉት፥ ሁለቱ የካንሰር  ዓይነቶች ሴቶችን በስፋት የሚያጠቁ በሽታዎች ናቸው። መንግሥት ህሙማን ለሌሎች የካንሰር ህመሞች ህክምና ከሚከፍሉት ገንዘብ ውስጥ 60 በመቶው ለታካሚዎች እንደሚመለስም ጠቁሟል። አዲስ ለሚጀምረው የነጻ ህክምና 1.6 ቢሊየን ዶላር መመደቡ ነው የተሰማው። የዓለም ጤና ድርጅት የህክምና ባለሙያዎች ሴኔጋል ያሰበችው እርምጃ በድህነት ምክንያት በበሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ ያግዛል ብለዋል። በአፍርካ እንደ ሩዋንዳ፣ ናሚቢያ እና ሲሼልስ ያሉ ሀገራት ነጻ የኬሞቴራፒ ህክምና እየሰጡ  መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም