በቤንሻንጉል ጉሙዝ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ ተመለከተ

50
አሶሳ ኢዜአ መስከረም 6 ቀን 2012- በተያዘው የትምህርት ዘመን በትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ በማድረግ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ የትከረት አቅጣጫ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር አሰታወቁ። የክልሉ 22ኛው ትምህርት ጉባኤ ዛሬ በአሶሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን እንደገለፁት በክልሉ በትምህርት ተደራሽነት ውጤት ቢገኝም ጥራቱ ግን አሽቆልቁሏል፡፡ "የባለሙያ ብቃት ማነስና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መቀዛቀዝን ጨምሮ ሌሎች ውስብስብ ጉዳዮች ለችግሩ ምከንያት ናቸው " ብለዋል ። በትምህርት ዘመኑ የትምህርት ጥራትን ማሻሻል የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የገለፁት አቶ አሻድሊ “ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ተቋማት አቅደን ልንሰራ ግድ ይለናል" ብለዋል፡፡” ባለፈው ዓመት በክልሉ በተከሰተ የጸጥታ ችግር ሃገር አቀፍ ፈተናዎች ጭምር እንዳይስተጓጎሉ ኃላፊነታቸውን የተወጡ አካላት መኖራቸውን አስታውሰዋል ። የክልሉ መንግስት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ቁርጠኛ ከሆኑ መሠል ባለድርሻ አካላት ጋር በአጋርነት እንደሚሰራ አመላክተዋል ። "በክልሉ ትምህርት ጉባኤ ላይ ስለተሳተፉ የትህምህርት ጥራት የሚረጋገጥ የሚመሥላችሁ የመንግስት አካላት ጨምሮ ሌሎች ተሳትፋችሁ ዝቅተኛ የሆነ ወገኖች ወደ ዘላቂ ሥራ ልትገቡ ይገባል" ሲሉ ርዕሰ መስተዳደሩ  አሳስበዋል፡፡ "የትምህርት ተቋማትን ሠላማዊ ማድረግ መሠረታዊ ጉዳይ ነው" ያሉት ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ኩዊ ናቸው፡፡ ቢሮው ዘንድሮ ከተመደበለት በጀት አብዛኛውን ለጥራት ማስጠበቅ  ተግባራት ማስፈፀሚያ የሚያውል መሆኑን ጠቁመዋል። የመምህራንን ብቃት ማሳደግና በየዘርፉ የውጤት ተኮር ምዘና ስርዓትን ለማስፈን የተጀመረው ጥረት እንደሚቀጥል ለአብነት ጠቅሰዋል ። የጉባኤው ተሳታፊዎች ለትምህርት ጥራት መሻሻል የሚረዱ የመፍትሔ ሃሳቦችን በማፍለቅ እንዲሳተፉ ኃላፊው ጠይቀዋል፡፡ ጉባኤው ነገም እንደሚቀጥል ታውቋል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም