በወላይታ ለኢንዱስትሪዎች ማስፋፊያ ከ136 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

68
ሶዶ ኢዜአ መስከረም 6 / 2012 ዓም በወላይታ ዞን ለኢንዱስትሪ ማስፋፊያ በተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከ136 ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ዋና አስተዳዳሪው አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ለኢዜአ እንደገለፁት በዞኑ ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም የስራ እድል ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል። እቅዱን ለማሳካት በተዘጋጀ የአንድ ቀን ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከ136 ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን ተናግረዋል ። ገቢው እየተሰበሰበ ያለው የእንጨት ዉጤቶችና የግንባታ ግብአቶች ማምረቻ እንዲሁም የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ለማቋቋም እንደሆነ አመላክተዋል ። በመንግስት ድጋፍ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ሽርክናና በባለሀብቶች ተሳትፎም ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም እንደ አማራጭ መቀመጡን ተናግረዋል ። "ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ይስፈልጋል" ያሉት አስተዳዳሪው ፕሮጀክቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል ። ከነሃሴ ወር 2011 ዓም ጀምሮ ለኢንዱስትሪዎች ማረፊያ የሚሆኑ ቦታዎች የመለየት፣ የማካለልና ሼዶች የማቆም ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል ። በኢንቨስትሜንት ለመሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች መሰረተ-ልማቶች የተሟሉለት ከካሳና መሰል ጉዳዮች ነጻ የሆነ ከ300 ሄክታር በላይ መሬት የዘጋጅቷል" ብለዋል ። እንደ አስተዷዳሪው ገለጻ ተሚቋቋሙት ኢንዱስትሪዎች ከ8 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል ይፈጠራል ። የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በዞኑ የሚታዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጥናት ለይቶ ለመፍትሄ መሰጠት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል ። "ዩኒቨርሲቲው በዞኑ ኢንዱስተሪዎችን ለማቋቋም እየተካሄደ ላለው ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ 30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል " ። እንደ ጽሬዝዳንቱ ገለጻ ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀከቱን በሙያም እየደገፈ ነው።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም