ለሆስፒታሉ እድሳት መደረጉ ሕሙማን የመንፈስና የስጋ ድሕነት እንዲያገኙ ያስችላል - ኢዜአ አማርኛ
ለሆስፒታሉ እድሳት መደረጉ ሕሙማን የመንፈስና የስጋ ድሕነት እንዲያገኙ ያስችላል
56
መስከረም 5/2012 የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እያካሔደ ያለው እድሳት ሕሙማኑን በመንፈስም ሆነ በስጋ ድሕነትን እንዲያገኙ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ የሐይማኖት አባቶች ገለጹ። የተለያዩ የሐማኖት ተቋማት አባቶች ዛሬ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕመምተኞትን ጎብኝተዋል። የሐይማኖት አባቶቹ የጨቅላ ሕፃናት፣ የእናቶች እንዲሁም የጽኑ ሕሙማን ክፍሎችን የጎበኙ ሲሆን የሆስፒታሉ መታደስ ሕሙማኑ የላቀና የተሻለ ሕክምና እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በክረምት ባስተላለፉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥሪ መሰረት በባለሃብቶች እየታደሰ መሆኑ ይታወቃል። ሆስፒታሉን ከጎበኙት ውስጥ የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ሕብረት የበላይ ጠባቂና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጉብኝቱ ብዙ መልካም ነገር ማየታቸውን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንትና የሐይማኖት ተቋማቱ ሕብረት የበላይ ጠባቂ ካርዲናል ብርሐነ ኢየሱስ ሱራፌል፤ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ፤ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዓመት ከግማሽ ሚሊዮን ለሚልቁ ሰዎች ሕክምና እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል።