አልጄሪያ ታህሳስ ላይ ምርጫ እንደምታካሂድ አስታወቀች

91

ኢዜአ፤ መስከረም 5/2012 አልጄሪያውያን በመጪው የፈረንጆቹ ታህሳስ 12 ቀን 2019 የሀገራቸውን ፕሬዚዳንት እንደሚመርጡ ታውቋል።

ምርጫ የሚካሄድበት ቀን በጊዜያዊ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብደልቃድር ቤንሳላ ይፋ ተደርጓል።

የአልጄሪያ ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አህመድ ጋይድ ሳላህ ሀገሪቱ ምርጫ የምታካሂድበት ጊዜ በይፋ እንዲነገር  ከሳምንታት በፊት ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ለሃምሌ 4/2019 ታቅዶ የነበረ ቢሆንም እጩዎች ባለመቅረባቸው ምክንያት መራዘሙ ይታወሳል።

ሀገሪቱን ለ20 ዓመታት የመሯት የ82 ዓመቱ አብደልአዚዝ ቡተፍሊካ ህዝባዊ ጫናው ሲበረታባቸው ባለፈው ሚያዚያ ላይ ስልጣን ለቀዋል።

ሀገሪቱን በጊዜያዊነት እንዲመሩ የተሰየሙት አብደልቃድር ሳላህ በሀገሪቱ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ተቋማዊ ለውጦች ይደረጉ በሚሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ጫና ውስጥ ወድቀዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም