የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ተስማሙ

93
ኢዜአ ጳጉሜ 6/2011 የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና የተቃዋሚ ኃይሎች መሪው ሬክ ማቻር በመጪው ህዳር ወር ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት መስማማታቸውን የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሳልቫ ኪር እና ሬክ ማቻር በሀገሪቱ በርካታ ዜጎችን ለሞትና ለመፈናቀል የዳረገውን የእርስ በእርስ ግጭት ለማስቆም ከአንድ ዓመት በፊት መፈራረማቸው ይታወሳል።
የተቃዋሚ ኃይሎች መሪው ማቻር ሰሞኑን በጁባ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል። የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ሚኬል ማኩዊ ሉቴ እንዳሉት ሁለቱ ተቀናቃኝ ኃይሎች በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ በመወያየት በመጪው የፈረንጆቹ ህዳር 12 ላይ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት ለመመስረት በመርህ ደረጃ ተስማምተዋል። የሀገሪቱ መንግሥት የታጠቁ ኃይሎችን ትጥቅ አስፈትቶ ለማዋሃድ በቂ በጀት የለኝም በማለቱ የአንድነት መንግሥት ለመመስረት ባለፈው ዓመት የተፈረመው ስምምነት ሳይተገበር ዘግይቷል። ምንጭ ሬውተርስ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም