የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመላ የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

84
ሰኔ 7/2010 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለመላ የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ ጨረቃ አመሻሹን በመታየቷ  1 ሺህ 439ኛው  የኢድ አልፈጥር በአል በነገው ዕለት ተከብሮ ይውላል፡፡ “የረመዳን ወር  የጾም፣ የጸሎት እና ከፈጣሪ ጋር የመገናኛ ልዩ ወር እንደመሆኑ መጠን፣ ኢድ አልፈጥርም፣ የፍቅር እና የበረከት፤ የይቅርታ እና የአብሮነት ድንቅ በአል” መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው አብራርተዋል፡፡ መንፈሳዊ በዓላትን በፍቅርና በጉጉት ማክበር የሚቻለው የሀገሪቱ ሰላም ሲረጋገጥ በመሆኑ መላ የእስልምና እምነት ተከታዮችና የኢትዮጵያ ህዝቦች በጠቅላላ ለሀገሪቱ “ሁለንተናዊ ለውጥ እና ህዳሴ”  የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታና የአንድነት እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሙሉ መልዕክት ከዚህ ያገኛሉ፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም