ኢትዮጵያና እስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል

81
ኢዜአ ነሃሴ 26/2011 በእስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአስራኤሉ አቻቸው ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ  ወቅት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እንዳሉት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የረጅም ግዜ ግንኙነት  በቀጣይ በግብርና፣ መስኖ፣ አይሲቲና በሌሎችም ዘርፎች ለሚኖረው ትብብር መሰረት ይጥላል:: በውይይታቸው ማብቂያም ባለ አምስት ነጥብ የጋራ መግባቢያ በአምባሳደሮቻቸዉ በኩል መፈራረማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል በዚሁ መሰረትም ፡-
  1. በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ትብብር በሀገራቱ ሕግና መመሪያ መሰረት በጋራ የበለጠ ለማጎልበት
  2. በግብርና ፣ በውሃ ፣ በመስኖ ልማት ፣ በጤና እና በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተፈረሙ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ትብብራቸውን ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል
  3. ሁለቱ ወገኖች የሳይበር ደህንነት ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና የጠፈር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ጨምሮ በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ ተጨማሪ ስምምነት (ቶች) ለመፈራርም የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለመመርመር
  4. የተፈረሙ ስምምነቶችን ተፈፃሚነት ለመቆጣጠር እና በአፈፃፀም ወቅት ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ስልቶችን ለመቀየስና
  5. በተቀመጠው ውስን የሀብት አቅም በሁለቱ አገራት መካከል የተደረጉ ስምምነቶችን አፈፃፀም ለመከለስና ለመከታተል ተስማምተዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም