አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆኑ

57
ሀዋሳ ነሐሴ 25 /2011 የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዘጠነኛ መደበኛ ጉበኤው የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በመሾምና ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በማጽደቅ ተጠናቀቀ። የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ እንዲደረግ በወሰነው መሠረት አቶ ርስቱ ይርዳውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ክልሉን እንዲመሩ ሾሟቸዋል። በተጨማሪም ለ2012 በጀት ዓመት 40 ቢሊዮን 56 ሚሊዮን 938 ሺህ 826 ብር አጽድቋል። በጀቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ3 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው። የበጀቱ ምንጭ ከፌዴራል መንግሥት ድጎማ፣ ከውጭ እርዳታና ከክልሉ ገቢ እንደሚሰበሰብ የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ ገልጸዋል ። ጉባዔው የአቶ ርስቱን ሹመት ያጸደቀ ሲሆን፣ቃለ መሃላም ፈጽመዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም