ታንዛኒያ የብሩንዲ ስደተኞች ሃገሯን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች

118
ኢዜአ ነሃሴ 22/2011 ታንዛኒያ 200 ሺ የሚሆኑ የብሩንዲ ስደተኞች አገርዋን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች፡፡ የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር የብሩንዲ ስደተኞች እኤአእስከ ጥቅምት 1/2019 ባለው ግዜ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሚኒስትሩ ካንጊ ሉጎላ በአሁኑ ወቅት በብሩንዲ ምንም ዓይነት የሰላም ችግር የለም የብሩንዲ ስደተኞች ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው ብለዋል፡፡ እስከ ጥቅምት 1 ባለው ግዜ ካልተመለሱ ግን ቢፈልጉም ባይፈልጉም በግድ ከአገራችን እንዲወጡ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ብሩንዲ እ.አ.አ 2015 ዓም ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን በአገሪቱ በሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይበተወዳዳሪነት እንደሚቀርቡ ባስታወቁበት ጊዜ በገጠማቸው ተቃውሞ የጀመረው አመጽ እስከ አሁን መረጋጋት ተስንዋታል፡፡ በታንዛኒያ ደቡብ ምዕራብ ኪጎማ ግዛት ንያሩጉሱ፣ንዱቱ እና ምተንደሊ በተባሉ የስደተኞች ካምፕ በርካታ ብሩንዳውያን ስደተኞች ተጠልለውይገኛሉ፡፡ ታንዛኒያ ስደተኞችን በሃይል አስገድዶ መመለስ የሚከለክለው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ስምምነት ከተቀበሉት አገራት አንዷ ናት፡፡ ሆኖም የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ካንጊ ሉጎላ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ቡሩንዲ ባለፈው ዓመትበየሳምንቱ 2 ሺ ስደተኞች ወደ አገርዋ ለመመለስ የገባችው ስምምነት እንዲተገበር አላደረገም የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡ የብሩንዲ ስደተኞች በበኩላቸው ወደ አገራቸው መመለስ እንደማይፈልጉ እየገለፁ ነው፡፡ የንኩሩንዚዛ መንግስት ግድያዎች እና ጠለፋዎች የመሳሰሉ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ይፈጽማል ፣ የታንዛኒያ መንግስት አሳልፎ ሊሰጠንአይገባም እያሉ ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት የቀጠናው ቃል አቀባይ ዳና ሂዩዝ ሁለቱም አገራት ዓለም አቀፍ ስምምነት እና የስደተኞች መብትእንዲያከብሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ እ.አ.አ 2017 ጀምሮ እስከ አሁን 75 ሺ ስደተኞች ወደ ብሩንዲ ማስመለስ የተቻለ ሲሆን በአንፃሩ አሁንም ቢሆን በመቶዎች የሚቆጠሩቡሩንዳውያን አገራቸው ጥለው እተሰደዱ ነው ፡፡ ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም