ጳጉሜ 2 የሠላም ቀን ምክንያት በማድረግ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ይካሄዳል

123
ነሀሴ 21/2011 ጳጉሜ 2 የሠላም ቀን ምክንያት በማድረግ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር እንደሚካሄድ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ። ጰጉሜን 2 በአገር አቀፍ ደረጃ በሚከበረው የሠላም ቀን 'ሠላምን እንትከል' በሚል መሪ ኃሳብ በሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል አስተባባሪነት ይካሄዳል። ይህንንም ተከትሎ ዛሬ የሠላም ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሯ ወይዘሪት ሄርሜላ ሠለሞን በሰጡት መግለጫ ቀኑን በማስመልከት የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ይካሄዳል ብለዋል። ከእለቱ በተጨማሪም ነሐሴ 26 ቀን ሕጻናት ወይም ልጆች በየትምህርት ቤቶቻቸው እንዲሁም ነሐሴ 30 ቀን ደግሞ አዋቂዎች በተለይም በጤና ተቋማት ችግኝ እንደሚተክሉ ተናግረዋል። በዋናው ዕለት ማለትም ጳጉሜ 2 ደግሞ  ችግኞች በተለያዩ አከባቢዎች እንዲተከሉ ይደረጋል ብለዋል። በአዲስ አበበ ደግሞ ከሠላም ሚኒስቴር እስከ ግዮን ሆቴል የእግር ጉዞ ይደረጋልም ብለዋል። ይህም በሁሉም ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ እንደሚሆን በማከል። በቀኑ የኅብረተሰቡን አብሮነት ሊያጎለብቱ የሚችሉ የቤተ-እምነት ሥነ-ሥርዓቶችና የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በተለያዩ አከባቢዎች እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ለማጉላት ይሰራልም ነው ያሉት። በዋነኝነትም ዝግባ፣ ወይራና ዋርካ የመሳሰሉ ችግኞች እንደሚተከሉ ነው የገለጹት ዳይሬክተሯል። ሚኒስቴሩም ይህንን የሚያደርገው መስከረም 10 የአየር ንበረት ለውጥን ታሳቢ በማድረግ ከሚከበረው የሠላም ቀን ጋር አብሮ ለማስተሳሰር መሆኑንም ገልጸዋል። ጳጉሜ 2 አገር አቀፍ የሰላም ቀን ተበተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሮ እንደሚውል እቅድ መያዙ ይታወሳል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም