የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች የሻይ እረፍታቸውን ወደ ጤና እረፍት ቀየሩ

48
አዲስ  አበባ  ነሀሴ 19/2019 የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች የሻይ እረፍታቸውን "የጤና እረፍት" በማለት ወደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ቀይረዋል፡፡ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች ከሰዓት በኋላ ያላቸውን የሻይ እረፍት "የጤና እረፍት" በማለት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ማሳለፍ ጀምረዋል። የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት ባለፈው መስከረም ይፋ እንዳደረገው ዓለም ህዝብ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ወይም ከአራት ስዎች አንዱ የጤናና አካል ብቃት እንቅስቀሴ አያደርግም። ይህም በመሆኑ በርካቶች አላአስፈላጊ ውፍትርና የጤና ችግር እያጋለጣቸው መሆኑን አመልክቷል። በተለይም  እንደ ስኳር፣ ደም ግፊትና ሌሎች በተላላፊ ላልሆኑ ሽታዎች በብዛት የተጋለጡ መሆኑን   መረጃው ጠቁሟል። የመረጃዎች እንደሚያመለክቱት አካል ብቃት ስፖርት በመስራት በኩዌት ህዝብ ከዓለም ሀገራት ዝቅተኛ ነት ተቀምጠዋል። የሜሪካና ሳውዲ አረቢያም ህዝቦች በአካል ብቃት ስፖርት ያላቸው ተሳትፎ ቅተኛ ከሚባሉ አራት ዝርዝር ውስጥ  ይገኛል። በአንጻሩ አፍሪካዊቷ ሀገር ዩጋንዳ የጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድርግ ከዓለም ቀዳሚ ሀገራት  ናት። ዩጋንዳ በጅማናዚየም ቤቶች ብቻ ሳይሆን ስዎች በሚሰሩበት ቦታ ተማሪዎች ደግም በትምህርት ቤት ውስጥ የአካል በቃት ስፖርት በመስራት ከዓለም አራት ቀዳሚ አድርጓታል። ከዩጋንዳ ቀጥሎ ሌላኛው አፍሪካዊት አገር ሞዛቢክም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድርገ በኩል ልምድ ካዳበሩ አገራት መካከል ተሰልፋለች። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያም የየህዝቡ አካል ብቃት እንቅስቃሴ  ዝቅተኛ መሆኑ ይነገራል። ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልምድ ማነስ በተጨማሪ   አየመጋገብ ባስርአት ባለመከተልም ሀአሪቷ አጠቃላይ ከሚሞቱት  ውስጥ 50 በመቶ በላይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎችና  ድንገተኛ አደጋ ምክንያቶች  መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ ። በጤና ሚኒስቴር  የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ዶክተር ተገኘ ተረጋሳ እንደሚሉት  ተላላፊ ያልሁኑ በሽታዎች ን ለመከላከል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ወሳኝ ነው። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድርግ የህዝቡ የእለት ከእለት ልምድ ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም መክረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ለጤና ጠቃሚ የሚባል የአመጋገብ ስርአትን መከተልም ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች ጤናቸውን በመጠበቅ አርእያ ሆነው ለመገኘት የሻይ እረፍታቸውን ወደ ጤና እርፍት ቀይረዋል ያሉት ዳይሬክተሩ ይሄው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የሌሎች ተቋማት ሰራተኞችም ይህንኑ አርአያ በመከተል ጤንነታቸውን እንዲጠብቁ አሳስበዋል። በአገርአቀፍደረጃምበወርአንድቀንየሚከናወነውከትራፊክነጻቀንበተለያዩከተሞችተግባራዊእየተደረገመሆኑንአስታውሰዋል። ይህ ተግባር በዋና ዋና የክልል ከተሞች የተጀመረ ቢሆንም አሁን ላይ ከ32 በላይ ከተሞች የአካል ብቃት እንቅቃሴ እያደረጉ ነው ብለዋል።ይበቀጣይ ሁሉም ከተሞች በተሞክሮውን በማስፋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልምድ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ይገባል ብለዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም