‘ቢቂላ’ የሽልማት ድርጅት የዚህ ዓመት ተሻላሚዎቹንና የክብር እንግዶቹን ይፋ አደረገ

174
አዲስ አበባ ኢዜአ ነሃሴ 18/2011 በአፍሪካ-ካናዳዊያን ማሕበረሰብ ዘንድ እውቅና ያተረፈውና በእውቁ አትሌት አበበ ቢቂላ ስም የተሰየመው ቢቂላ የሽልማት ድርጅት ስድስተኛ የሽልማት መርሀ ግብሩን መስከረም 10 ካናዳ ቶሮንቶ ያደረጋል። ድርጅቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ ‘ቢቂላ ሽልማት' በካናዳ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በትምህርት፣  በንግድ ስራና በበጎፈቃድ ዘርፍ ጎልተው እንዲወጡ ለማበረታታት የተቋቋመ ገለልተኛ ድርጅት ነው። በዚህ ዓመት መርሀ ግብሩም የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሽልማቱ ለታዋቂና ለየት ያለ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ግለሰቦች እንዲሁም በትምርታቸው ላቅ ያለ ውጤት ያገኙ ወጣቶች እውቅና የሚያገኙበት መሆኑም ታውቋል። በዚሁ መሰረት የዚህ ዓመት ‘የአንጸባራቂ ኮኮብ ሽልማት’ ዘርፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ለነበሩት አክሊሉ ሀብተወልድ የሚሰጥ ሲሆን እሳቸው በሕይወት እያሉ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ለሕዳሴዋና ኢትዮጵያን ወክለው ለባረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሆን የተደረገ ነው። ‘የሕይወት ዘመን ሽልማቱ’ ደግሞ ለኮለኔል ስምረት መድህኔ የሚሰጥ ሲሆን ሽልማቱ እሳቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይልንና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመለወጥ ላባረከቱት ልዩ እስተዋፅኦ መሆኑ ታውቋል። የትነበርሽ ንጉሴ ደግሞ በሙያቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም በአካል ጉዳተኛነት ሁሉን አቀፍ አካታችነትን ለማስገንዘብ በሰሩት ስራ ተሸላሚ ይሆናሉ። ኤልያስ ወንድሙ፣ ዶክተር ኢብራሂም ይመርና ተሰማ ቢተው ደግሞ በየተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ በዚህ ዓመት ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ የሽልማቱ እጩ ሆነው ቀርበዋል። የ2019 ዓ.ም ‘ቢቂላ’ ስኮላርሺፕ ሽልማት ደግሞ ሶሊያና ገድሉ፣ ቅዱስ መክብብ፣ አንጄል አየለና ቤቴልሄም ሳምሶን የእድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። የዚህ ዓመት የመርሃ ግብሩ ንግግር አድራጊ ሳይካትሪስት፣ ደራሲና አነቃቂው ዶክተር ምሕረት ደበበ ናቸው። በክብርእንግድነትደግሞየብላክሪህኖግሩፕዋናስራአስኪያጅናየዳይሬክተሮችየቦርድአባልሚሚአለማየሁንግግርያደርጋሉ። የኢቢኤስቴሌቪንሾውአዘጋጇሔለንመስፍንደግሞመድረኩንትመረዋለችተብሏል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም