የቱኒዝ ካርቴጅ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደገና ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

112
ነሐሴ 16/2011 የቱኒዚያ መንግስት በደህንነት ስጋት ዝግ ሆኖ የቆየውን የቱኒዝ ካርቴጅ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመክፈት መወሰኑን ተነገረ፡፡ ውሳኔው የተካሄደው የቱኒዝያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሴፍ ቻሃድ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂቻም ፎራቲ እና የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ሂቻም ቤን አህመድ ባካሄዱት ስብሰባ እንደሆነ የመንግስታዊው መግለጫ ያሳያል ሲል ዘገባው አስፍሯል፡፡ ከተሰብሳቢዎቹ መካከል ሁለቱ ሚኒስትሮች በአውሮፕላን ማረፊያው የመከላከያና ደህንነት እርምጃዎችን ለማጠናከር በሚያስችሉ ቴክኒካል ዘዴዎች ላይ በሪፖርት መልክ አቅርበዋል ሲልም ዘገባው አክሏል፡፡ በቱኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒስ የተፈፀሙ ሁለት የሽብር ጥቃቶችን ተከትሎ የሀገሪቱ የፀጥታ ባለስልጣናት ትዕዛዝ ከሰኔ 27/2019 ጀምሮ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያው ተዘግቶ እንደነበርም ዘገባው አስታውሷል፡፡ (ሲ ጂ ቲ ኤን )
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም