አሜሪካ በ8 ቢሊዮን ዶላር 66 ኤፍ-16 ተዋጊ ጀቶችን ለታይዋን ልትሸጥ ነው

121
ኢዜአ ነሃሴ 15/2011 የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በ8 ቢሊዮን ዶላር 66 ኤፍ -16 ታዋጊ ጀቶችን ለታይዋን ለመሸጥ ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ ፡፡ የአሜሪካ ለታይዋን ተዋጊ ጀቶች መሸጧ ቻይናን ሊያስቆጣ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡
ዘመናዊውን ተዋጊ ጀት አሜሪካ ለታይዋን ለመሸጥ ውሳኔ ማሳለፏን ተከትሎ “ታይዋን የዚህ ዘመናዊ ጀት ባለቤት ልትሆን ነው” ሲል የአሜሪካ ስቴት ዲፖርትመንትን ጠቅሶ አልጄዚራ ዘግቧል ፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ እንደተናገሩት የዘመናዊ ጀት ሽያጩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀድሞ እውቅና ያገኘ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ይህ የጦር ጀት ሽያጭ ቀድሞ የአሜሪካ ፖሊሲ የነበረ እንደሆነ የተናገሩት ፖምፒዮ በቀላሉ አሜሪካ እየተከተለች ያለችው ከዚህ ቀደም ለሁሉም እያደረገች ያለውን ነው ብለዋል፡፡ ይህ ድርጊት ቀድሞ የታቀደ በመሆኑም ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት እንደማያሻክረው በመጥቀስ፡፡ የአሜሪካ የአለም አቀፍ ግኑኝነት ኮሚቴ ሃላፊ ጂም ሪሲች የአሜሪካ የሪፖፕሊካን ፓርቲ የጦር ጀት ሽያጩን በጸጋ የሚቀበለው እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ ይህ ሽያጭ ታይዋን የአገሪቷን የአየር ክልል ከፍተኛ ጫና እያደረገችባት ከምትገኘው ቻይና ለመከላከል ከፍተኛ አቅም የሚፈጥርላት ይሆናል ብለዋል፡፡ የቻይና ጦር የታይዋን አየር ክልል የማጥቃትና የመውረር ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ ታይዋን የአይር ሃይሏን የማጠናከር እቅዷ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ቤጂንግ ታይዋን የቻይና አካል መሆኗንና የመቀላቀያዋ ቀንን የምትጠብቅ ስትሆን ታይዋን እራሷን የምታስተዳድር የአሜሪካ ወዳጅ መሆኗን አልጂዚራ ዘግቧል፡:
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም