የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ያካሂዳል

50
ጅግጅጋ ነሐሴ 13 ቀን 2011  የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አራተኛ አስቸኳይ ጉባዔውን ነገ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብዱረሺድ ዓሊ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ምክር ቤቱ ለአንድ ቀን በሚቆየው ጉባዔ በሁለት ረቂቅ ዓዋጆች ላይ ተወያይቶ ያጸድቃቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ  ከሚመለከታቸው ረቂቅ ዓዋጆች አንደኛው የክልሉን አስፈጻሚ አካላት እንደገና ለማደራጀት፣ተግባርና ኃላፊነታቸውን መወሰንን የሚመለከተው ነው። በተጨማሪም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ ዓዋጅም መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኃላፊው አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም