የድሬዳዋ ሪፈራል ሆስፒታልን ዩኒቨርሲቲው ተረከበው

177

ድሬዳዋ ነሐሴ 11/ 2011 በድሬዳዋ ከተማ በ334 ሚሊዮን ብር ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሪፈራል ሆስፒታል የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተረከበው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት የርክክብ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የአስተደደሩ ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታሉን በፍጥነት በማጠናቀቅ የተሻለና ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ለኅብረተሰቡ መስጠት አለበት።

ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታሉን መረከቡ የተጓተተውን ግንባታ በአጭር ጊዜ አጠናቅቆ በድል ጮራ ሆስፒታል የሚገኘውን መጨናነቅ ያቃልለዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪምየኅብረተሰቡንችግሮችየሚፈቱጥናትናምርምሮችንበማድረግመሠረታዊለውጥማምጣትእንደሚያስችለው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሕክምናተማሪዎችጥራቱንየጠበቀስልጠናለመስጠትእንደሚያስችለውም ምክትል ከንቲባው አስታውቀዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ያሬድ ማሞ በበኩላቸው አስተዳደሩ በዩኒቨርሲቲው ላይ ያለውን እምነት በተግባር ለመተርጎም ጠንካራና የተቀናጀ እንቅስቃሴ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ቀሪ የግንባታሥራዎችን በአንድ ዓመት በማጠናቀቅ ሆስፒታሉ የሚጠበቅበትን አገልግሎት እንዲሰጥ ርብርብ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡

‹‹ዩኒቨርሲቲው ያቀደውን እስከ መጨረሻ እውን የሚያደርገው ከአስተዳደሩ ካቢኔና ከአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን ነው›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፉአድ ከድር በበኩላቸው ቢሮው ከዩኒቨርሲቲው ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የሆስፒታሉ ግንባታ መጓተት ቢያጋጥመውም፤ አሁን ወደ ወደ መገባደድ ደረጃ መድረሱን ገልጸዋል፡፡

ሆስፒታል የሚጠበቅበትን አገልግሎት እንዲሰጥ ዩኒቨርሲቲው መረከቡ ተገቢ መሆኑን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

የቢሮው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለ አምስት ፎቁ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታው 62 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ቀሪዎቹ የኤሌክትሪክና የማጠናቀቂያ ተግባራት ናቸው፡፡

የድሬዳዋ ሪፈራል ግንባታ መጓተትን አስመልክቶ መፍትሄ እንዲፈለግለት ኢዜአ ተደጋጋሚ ዘገባዎችን መስራቱ ይታወሳል፡፡