7ኛው የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት ፕሮግራም የምዘናና የልየታ ውድድር ሊካሄድ ነው

63
አርባ ምንጭ (ኢዜአ) ነሀሴ 10ቀን 2011-ሰባተኛው አገር አቀፍ የታደጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት ፕሮግራም የምዘናና የልየታ ውድድር ከነገ ጀምሮ በአርባ ምንጭ ከተማ ይካሄዳል። የአርባ ምንጭ ከተማ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌሾ ጌሎ ለኢዜአ እንዳሉት ውድድሩ የሚካሄደው በፌደራል ስፖርት ኮሚሽን አስተባባሪነትና በደቡብ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት ነው። ውድድሩ በአርባ ምንጭ ከተማ ከነሐሴ 11 እስከ 26 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድም አመልክተዋል፡፡ እንደኃላፊው ገለጻ የውድድሩ ዓላማ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ታዳጊ ወጣቶችን በመመልመል ወደተለያዩ አካዳሚዎች በማስገባት በተለያዩ ክለቦች ማስመረጥ ነው፡፡ ለ16 ቀናት በሚካሄደው የስፖርት ውድድር አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ ከዘጠኙም ክልሎች 5ሺህ የሚጠጉ ስፖርተኞች በ17 የስፖርት አይነቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም