የቀድሞው የሱዳን የመረጃና ደህንነት ሃላፊ ሳላህ ጎሽ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ

80
ኢዜአ ነሃሴ 9/2011 ሳላህ ጎሽ በስልጣን ዘመናቸው በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጃቸው እንዳለበት አሳማኝ መረጃ በማግኘቴ ነው እገዳውን የጣልኩት ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ ሳላህ ጎሽ የሱዳን የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃላፊ በነበሩበት ጊዜ በሰዎች ላይ በሚፈጸሙ የማሰቃያ ድርጊቶች እጃቸው አለበት።
የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ ቤተሰቦችም ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ክልከላ ተጥሎባቸዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒኦ ሱዳን ውስጥ በሲቪል አስተዳደር ለሚመራ የሽግግር መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርጉ በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። ኦማር ሀሰን አል በሺርን ከስልጣን ያወረደው የሱዳን ጦር የሽግግር ምክር ቤት በማቋቋም ሀገሪቱን ሲመራ ቆይቷል። ወታደራዊ ምክር ቤቱ እና የተቃዋሚዎች ጥምረት ከ10 ቀናት በፊት ለ3 ዓመት የሽግግር ጊዜ የሚጸናውን የጋራ አስተዳደር ለመመስረት እና ለስልጣን ክፍፍል መፈራረማቸው ይታወሳል። ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም