የደርባን ከንቲባ እና ባልደረቦቻቸው ከስራ ተሰናበቱ

67
ኢዜአ ነሃሴ 8/2011 የደቡብ አፍሪካ ገዥ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) በሙስና ፣ በማጭበርበር ወንጀል እና በምዝበራ የተከሰሱትን የደርባን ከንቲባ ከስራ ማሰናበቱን ቢቢሲ ዘገበ። ልዩ የስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባን ተከትሎ ከንቲባ ዛንዲሌ ጉሜዴን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከስራ እንዲሰናበቱ ማድረጉን የደርባን ከተማ የኤ ኤን ሲ ፅ/ቤት ገልጿል። ልዩ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት ከንቲባ ጉሜዲ ስለሆነው ጉዳይ ከመግለፅ እንደተቆጠቡ ቢቢሲ ጠቁሞ በስብሰባው ወቅት የተላለፈው ውሳኔ ላይ ተቃውሞ ያቅርቡ አያቅርቡ ግልፅ እንዳልሆነ ዘግቧል። ከንቲባዋ ከዚህ ቀደም ከመንግስት ኮንትራት ጋር ተያይዞ ከፈፀሙት የ14 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሙስና ክስ ጋር ተያይዞ በዚህ አመት በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ዘገባው አክሏል። የቀድሞው ከንቲባ መታሰር በደጋፊዎቻቸው ተቃውሞ አስነስቶ የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ ከንቲባዋ በተወሰኑ ቡድኖች ኢላማ ሆነዋል ብሏል ዘገባው፡፡ የወይዘሮዋ የሙስና ጉዳይ በቀጣይ አመት ጥር ወር ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ቢቢሲ በዘገባው ማጠቃለያ ላይ አመልክቷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም