የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ

178
ነሐሴ 7/2011 አገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤትን ይፋ አደረገ። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚያብሄር እንደገለጹት፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ  app.neaea.gov.et በመግባት ማወቅ ይችላሉ። የመፈተኛ ቁጥራቸውን አድሚሸን በሚለው ሳጥንውስጥ በማስገባት ውጤታቸውን  መመልከት ይችላሉ ብለዋል። በሞባይል አጭር የፅሁፍ መለእክት (SMS) 8181 id በማለት  የሚያዩበት አማራጭ መመቻቸቱንም ገልጸዋል። በ2011 ዓ.ም የትምህረት ዘመን 319 ሺህ 264 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ ሲሆን 59 ተማሪዎች ከ600 መቶ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ዘንድሮ 645 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡም ታውቋል። የዘንድሮው ውጤት ካለፉት ዓመት ጋር ሲነፃፀር መካከለኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ  ሲሆን ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 48 ነጥብ 59 በመቶ ናቸው። በፈተና ስነ ስርአት ጥሰት ምክንያት በቀረበባቸው ሪፖርት የ68 ተማሪዎች ውጤት መሰረዙንም አቶ አርአያ ገልጸዋል። ከአራት ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና ቤኒሻንጉል) የ864 ተማሪዎች ውጤት ለተጨማሪ ማጣራት እንዲያዝ ተደርጓል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም