በአፍሪካ ሩሲያ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በመሪዎቿ እንደምትወከል አምባሳደር አለማየው ተገኑ አስታወቁ

70
ነሐሴ 7/2011  በሩሲያ የኢትዮጵያ አማባሳደር የሆኑት አለማየሁ ተገኑ ስፑቲኒክ ለተባለ ሚዲያ እንደገለፁት ከሆነ ኢትዮጵያ በመሪዎቿ ደረጃ ቀጣይ በሚካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ ላይ እንደምትወከል ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለው ዘመን ተሸጋሪ መልካም ግንኙነት ለአፍሪካ-ሩሲያ ግንኙነትም  እጅግ አስፈላጊና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነም በመረጃው ሰፍሯል፡፡ ኢትዮጵያ ቀጣይ የሚካሄደውን ስብሰባ  እንደ ስትራቴጂካዊ ስልት አድርጋ ትወስደዋች መባሉንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡ ኢትዮጵያ በስብሰባው ወቅት በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ በፕሬዚደንቷ ወይም በጠቅላይ ሚኒስትሯ ልትወከል እንደምትችም አምባሳደሩ መናገራቸውን በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ አምባሳደር አለማየሁ ሲቀጥሉም ሩሲያ የአፍሪካን የመሰረተ ልማት ዘርፍ በመደገፍ በባቡር መንገድ ግንባታ፣ በአይሲቲ ዘርፍና የተፈጥሮ ሃብት በማውጣት ሰፊ ስራዎች እንደምትሰራ ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም ዓለም አቀፉን ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ አፍሪካ ከሩሲያ ጋር በትብብር እንደምትሰራም አስታውቀዋል፡፡ የመጀመሪያ ነው የተባለው የአፍሪካ ሩሲያ ስብሰባና የንግድ መድረክ በሩሲያዋ የሪዞርት ከተማ ሶቺ እ.አ.አ. ከጥቅምት 23-24/2019 ድረስ ሊካሄድ የሁለት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተይዞለታል ተብሏል፡፡ በዝግጅቱ ላይም ወደ 40 የሚጠጉ የሃገር መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም