በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባና የመረጃ ልውውጥ ላይ የቅንጅት አሰራር ክፍተት በስፋት ይታያል

101
ነሀሴ 1/2011 በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባና የመረጃ ልውውጥ ላይ የቅንጅት አሰራር ክፍተት በስፋት እንደሚታይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ባያደረገው ጥናት ጠቆመ ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ የወሳኝ ኩነትን ምዝገባ አፈጻጸምን አስመልክቶ ባደረገው ጥናት ላይ ዛሬ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። ጥናቱ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት አፈጻጸም፣ ተግዳሮቶችና የተገልጋዩን ህብረተሰብ የግንዛቤ ደረጃ በጥናት ለመለየትና ግብረ መልስ በማግኘት የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል። በጥናቱ በየካ፣ አዲስ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ነፋስ ስልክ ላፍቶና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ወረዳዎች በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ ባህርዳር፣ ሐረርና ጋምቤላ ከተሞች በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሚገኙ ሰራተኞችና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ተገልጋዮች ተካተዋል። እንዲሁም ከዕለት ተዕለት ስራቸው ጋር የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ከሚያካሄዱ ተቋማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፍትህ አካላት፣ ሆስፒታሎች(የግልና መንግስት) እንዲሁም ሌሎች በጥናቱ የተካተቱ አካለት ናቸው። ጥናቱ የአንድ ወር ጊዜ መፍጀቱንና በጥናቱ የተሳተፉ ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሙያተኞች እና ተገልጋይ ህብረተሰብን በማጠቃለል 711 ሰዎች በጥናቱ ናሙናነት እንዲሳተፉ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት እና የህዝብ አስተያየት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት የጥናት ባለሙያ አቶ ኤልያስ ጅብሪል በጥናቱ ግኝት አማካኝነት በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባና የመረጃ ልውውጥ ላይ የቅንጅት አሰራር ክፍተት በስፋት እንደሚታይ ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት በተቋማትና በፌደራል ኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ መካከል የመረጃ ልውውጥ ላይ ክፍተት እንዳለም ጠቅሰዋል። በተገልጋዮች በኩል በሲስተም መቆራረጥ ምክንያት የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ እንዳልሆነና የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሰራተኞች በደመወዝና በጥቅማ ጥቅም ምክንያት ከፍተኛ የስራ ፍልሰት እንደሚታይበትም ተናግረዋል። በፌደራል ኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በኩል ጥናቶችን በማድረግ የአሰራር ችግሮቹን ለመፍታት የሚደርገው ጥረት በጠንካራ ጎን የሚነሳ ነው ብለዋል። የጥናት ባለሙያው አቶ ኤልያስ ጅብሪል በጥናት ግኝቱ መሰረት የሚከተሉትን ምክረ ሀሳቦችንም አቅርበዋል። በፌደራል ኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ኤጀንሲው የጥናቱን ግኝቶች  እንደ ወሳኝ ግብዓት እንደሚወስዳቸውና ለቀጣይ ስራም የሚገለገልበት እንደሆነ ገልጸዋል። መንግስት ለወሳኝ ኩነት ምዝገባ ያለው የፖለቲካ ቁርጠኝነት መልካም የሚባልና ለስራ ማስኬጃ አስፈላጊውን በጀት እየመደበ መሆኑንም ተናግረዋል። በጥናቱ ዙሪያ ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተዋል። አቶ ቴድሮስ ቦጋለ የፌደራል ኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የኬላ ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ መኮንን የፌደራል ኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ በራሱ ተነሳሽነት ጥናቱን በማድረግ ላሳየው ተነሳሽነት ከምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ምስጋናና አድናቆት ተችሮታል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ከዚህ በፊት በምግብ ዋስትና፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ በፍትህ አሰጣጥና በመንግስት ተቋማት የድረ-ገጽ አገልግሎት ላይ ጥናቶችን አድርጎ ከባለድርሻ አካላት ጋር መምከሩ የሚታወስ ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም