በግብፅ የመኪና ግጭት ያስከተለው ፍንዳታ ለ19 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል

90
ኢዜአ ሀምሌ 29/2011 በካይሮ ብሄራዊ የካንሰር ኢንስቲቲዩት አቅራቢያ የደረሰው የመኪና ግጭት ባስከተለው ፍንዳታ 19 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 30 መቁሰላቸውን ነው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡ የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር በበኩሉ አንድ በፍጥነት የሚሄድ መኪና ከሌላው ጋር በመጋጨቱ ፍንዳታውን አስከትሏል ብሏል፡፡ ነገር ግን ግጭቱ ብቻውን ትልቅ ፍንዳታ ለምን እንዳስከተለ እስካሁን ግልፅ አለመሆኑንም ተናግረው አደጋው በመኪኖቹ ግጭት ብቻ መድረሱም አለመታወቁን ገልፀዋል፡፡ አደጋውን ተከትሎ የተለቀቁ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት በርካታ መኪኖችን ሲያቀጣጥል የነበረውን መጠነ ሰፊ እሳት የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ሊቆጣጠሩት ሲሞክሩ ተስተውለዋል፡፡ የካንሰር ህክምና ኢንስቲቲዩት ውስጥ ያሉ ለቀው የወጡ ሲሆን በታዋቂው አደባባይ ታኺር አቅራቢያም መሆኑ ታውቋል፡፡ ከሆስፒታሉ በተቃራኒ ጎን የሚገኙት የባንክ ጥበቃ አብድል ራህማን ሞሃመድ እንዳሉት” በአካባቢው ፍንዳታውን ሰምተናል በአፋጣኝም መግቢያ በሮቹን ዘግተናል” ብለዋል፡፡ የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር የቆሰሉ ሰዎች ወደ ህክምና መወሰዳቸውንም ገልጿል፡፡ የግብፅ አቃቤ ህግ የአደጋውን መንስኤ በመመርመር ላይ ሲሆን ለሮይተርስ የዜና ወኪል የተናገሩ ምንጮች ከመንግስት አካል ፍንዳታው ጥቃት መሆኑን አለመገለፁን ተናግረዋል፡፡ መርማሪዎች፣የወንጀል መርማሪ ላብራቶሪ እና የቦምብ ኤክስፐርቶች ፍንዳታው የደረሰበት ቦታ መገኘታቸውን ምንጮች ለአልጀዚራ ተናግረዋል፡፡ በግብፅ የመኪና አደጋ የተለመደ እንደሆነ የገለፀው የአልጀዚራ ዘገባ 8 ሺህ ግጭቶች ባለፈው አመት መመዝገባቸውንና ይህም ለ3 ሺህ ሰዎች ሞትና  ለ12 ሺህ ሰዎች መቁሰል ምክንያት መሆኑን አስነብቧል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም