የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ በጅግጀጋ ቅርንጫፉን ከፈተ

69
ጅግጅጋ ሰኔ 5/2010 የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ለኢትዮ- ሶማሌ ክልል የመጀመሪያ የሆነውን ቅርንጫፍ ዛሬ በጅግጀጋ ከተማ ከፈተ፡፡ ቅርንጫፉን መርቀው የከፈቱት የሶማሊ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዮሃንስ ተክሉ ናቸው፡፡ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የቅርንጫፉ መከፈቱ ለክልሉ ህዝብ እና መንግስት የረዢም ጊዜ ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው፡፡ በዚህም የክልሉ ነዋሪዎች ያለምንም መንገላታት አገልግሎቱን በአቅራቢያቸውና በፍጥነት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም