ኬኒያ የተባበሩት መንግስታት አልሻባብን በሽብር ቡድን እንዲፈረጅላት ጥያቄ ልታቀርብ ነው 

64
ኢዜአ ሀምሌ 24/2011የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን አልሻባብ በተባበሩት መንግስታት በሽብር ቡድን የሚፈረጀው ከሆነ ፅንፈኛውን ቡድን በተሻለ መዋጋት ያስችላል ብላለች ኬኒያ ፡፡ ዘ ኢስት አፍሪካን ይዞት በወጣው ዘገባ ኬኒያ ለተባበሩት መንግስታት ፀጥታው ምክር ቤት አልሻባብ በሽብር ቡድን እንዲፈረጅላት ጥያቄ ታቀርባለች፤ይህም ፅንፈኛውን ቡድን በተሻለ ለመዋጋት ያግዘኛል ብላለች፡፡ “ጥያቄውን ለተባበሩት መንግስታት በይፋ የምናቀርብ ይሆናል፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም የተመድ ሪዞሊሽን 12 67 መሰረት በማድረግ  የሽብር ቡድኑ እንዲፈረጅ ድጋፏን እንሻለን ይህም የሽብር ቡድኑን በመዋጋት አለም አቀፍ ጥረቱን ያጠናክራል” ያሉት የኬኒያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፒኤስ ማቻሪያ ካማኡ ናቸው፡፡ ሚኒስትሩ እንዳሉት አልሻባብ ቀውስ እየፈጠረ ያለው በኬኒያ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ነው ፡፡ የተመድ የፀጥታ ምክርቤት የሽብር ቡድኑ ላይ ማእቀብ ከጣለ ከሽብር ቡድኑ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት አቅም ያሳጣል ብሏል ዘገባው፡፡ ምንጭ ፡አፍሪካን ኒውስ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም