"ዛድ" በሚል ስያሜ በምስረታ ላይ የሚገኘው ከወለድ ነፃ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ ሊጀምር ነው

57
አዲስ  አበባ  ሀምሌ 19/2011 "ዛድ" በሚል ስያሜ በምስረታ ላይ የሚገኘው ከወለድ ነፃ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ። ባንኩ ሥራውን የሚጀምረው በአንድ ቢሊዮን ብር መዋእለ ንዋይ ነው ተብሏል። ባንኩትናንትበሰጠውመግለጫባንኩንለመክፈትየሚያስችለውንፍቃድከኢትዮጵያ ብሔራዊባንክማግኝቱንጠቅሷል። ባንኩ በኢስላሚክ ባንኪንግ፣ በፋይናስ፣ ኢንቨስትመንት፣ ዓለም አቀፍ ንግድና በመሳሰሉት ተያያዥ ሙያዎች እውቀትና ልምድ ባላቸው ግለስቦች መቋቋሙን የባንኩ ማኔጂንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙኒር ሁሴን ገልጸዋል። ዛድ ባንክ ሥራውን የሚጀምረው በአንድ ቢሊዮን ብር መዋእለ ንዋይ መሆኑንም አቶ ሙኒር ተናግረዋል። ባንኩ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ለማበረታታት የሚያስችል መሆኑንም አመልክተዋል። በዘርፉ ብቁ የሰው ኃይል ለመፍጠርም በኢስላማዊ ባንክና ፋይናሲንግ መስኮች የስልጠና ማዕከል ለማቋቋም ልምድ ካለቸው ዓለም አቀፍ የትምህርትና ተቋማት ጋር መስማማቱንም ተናግረዋል። በመጪው ቅዳሜ ሐምሌ 20 ቀን 2011 ዓም የአክሲዮን ሽያጭ የሚጀመር መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሙኒር እያንዳንዱ አክሲዮንም የአንድ ሺህ ብር ዋጋ አለው ብለዋል። ባንኩስራውንሲጀምርለ400ዜጎችየሥራእድልየሚፈጥርሲሆንአገልግሎቱእያደገሲሄድተጨማሪየሰውኃይልእንደሚቀጥርምአመልክተዋል። ባንኩከወለድነፃየሆነየባንክአገልግሎትከመስጠትባሻገርበምጣኔኃብታዊናማህበራዊየልማትመስኮችበመሳተፍማህበራዊኀላፊነትንየመወጣትዓላማምአለውተብሏል። በኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚፈቅደው አዋጅ የወጣው ከአስር ዓመት በፊት ነው። በዚህም መሰረት በአገሪቱ የሚገኙ የንግድ ባንኮች የወለድ ነጻ የመስኮት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ተመሳሳይ ዓላማ ያለውና 'ሂጅራ' በሚል ስያሜ የሚጠራ ከወለድ ነፃ ባንክ አክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን ከሳምንት በፊት አስታውቋል። ሂጅራ ባንክ የሚቋቋመው በተመሳሳይ አንድ ቢሊዮን ብር የተመዘገበ መዋእለ ንዋይ መሆኑም ተመልክቷል። በኢትዮጵያ የባንክ ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የአገሪቱ አጠቃላይ የባንኮች ኃብት 800 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ይነገራል። ይህ አሃዝ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት 15 ቢሊዮን ብር ብቻ እንደነበርም እንዲሁ።                          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም