ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከዓለም ምግብ ፕርግራም ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ ጋር ተወያዩ

115
ሀምሌ 19/2011 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከዓለም ምግብ ፕርግራም ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያዩ። ውይይታቸውም ድርጅቱ ለኢትዮጵያ የሚያደርግውን ድጋፍ ማጠናከር በሚያስችሉ  ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የዓለም ምግብ ድርጅት በምግብ ዋስትና፣ ስነ ምግብ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ትግበራና መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። ከውይይቱ በኋላም ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ  ጋር ችግኝ ተክለዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም