ሶዴፓ የመሪነት ሚናውን እንደሚያጠናክር ሊቀመንበሩ ገለጹ

68
ጅግጅጋ ሐምሌ 17 / 2011  የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሶዴፓ) ሕዝቡን የመምራት ሚናውን እንደሚያጠናክር ሊቀመንበሩ ገለጹ። የፓርቲው 21ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በጅግጅጋ ከተማ  በመከበር ላይ ነው። ሊቀመንበሩ አቶ አህመድ ሺዴ በዓሉ ላይ ባቀረቡት ንግግር እንዳሉት ፓርቲው የክልሉን ሕዝብ ለሁለንተናዊ ዕድገት ለማብቃት አስተባብሮ መምራቱን ይቀጥላል። "ፓርቲው በአገራዊ ለውጡና የፌዴራል ሥርዓቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአመራሪነት ሚናውን መወጣቱን ይቀጥላል"ብለዋል። ፓርቲው ከተመሰረተበት 1990 ጀምሮ የክልሉን ሕዝብ አንድነት በመጠበቅ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን አቶ አህመድ አስታውሰዋል። በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ)፣የህዝባዊ  ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ)፣የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ(ሐብሊ)ና የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ(ኦብነግ)ተወካዮችና አመራሮች ለፓርቲው የአጋርነት መግለጫዎች ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በበዓሉ ላይ በርካታ የፓርቲው አባላት ደጋፊዎችና እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም