ትምህርት ቤቱ ግማሽ ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ቁሳቁሶችን በድጋፍ አገኘ

72
አምቦ (ኢዜአ) ሐምሌ 16 / 2011 በምዕራብ ሸዋ ዞን የኢጃጂ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት ግማሽ ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የትምህርት ቁሳቁሶችን በድጋፍ አገኘ። የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ማህበር አባላት ድጋፉ የደረጉትን ቁሳቁስ ትላንት አሰርክበዋል። የማህበሩ አባላት  ድጋፍ ካደረጓቸው የትምሀርት ቁሳቁሶች መካከል 17 ኮምፒውተሮች፣ 448 የመማሪ መጽህፍት እንዲሁም ደብተሮችና ስክሪብቶዎች ይገኙበታል ። በአካል ተገኝተው ድጋፉን ካበረከቱ አባላት መካከል አቶ ነጋሽ ባጫ እንደገለፁት ድጋፉ የትምህርተ ቤቱን የማስተማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለማቃለል የተደረገ ነው ። “በተጨማሪም በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ያለባቸው ተማሪዎች ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጎሉ ለመደገፍ ነው” ብለዋል ። አቶ ጸጋየ ደበላ የተባሉ የማህበሩ አባል በበኩላቸው በትምህርት ቤቱ የስፖርት ትምህርትና እንቅሰቃሴን የሚያጠናክሩ ድጋፎች እንደሚደረግ አመላክተዋል ። የኢሉ ገላን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ከበርኩ እንዳሻው የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር አባላት ያደረጉት ድጋፍ ለሌሎች አርአያ መሆኑን በመጥቀስ ምስጋና አቅርበዋል ።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም