የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ምክር ቤት ጉባኤ በመጪው እሮብ ይጀመራል

69
ሰመራ ኢዜአ ሀምሌ 15/2011  የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የስራ-ዘመን ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ በመጪው እሮብ በሰመራ ከተማ እንደሚጀምር የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር  አቶ አሊሚራህ ሙሳ እንደገለጹት ጉባኤው በሶስት ቀናት ቆይታ የ2011 በጀት ዓመት  አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ይወያያል፤ የተያዘው ስራ ዘመን  በጀት መርምሮ እንደሚያጸድቅ  ይጠበቃል። ሐምሌ 17/2011 ዓ.ም የሚጀምረው ጉባኤው  በተጨማሪም የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲት መስሪያ ቤትን ሪፖርት ያዳምጣል። የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  ምክር ቤት 96 አባላት እንዳሉት ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም