ሞቃዲሾ ውስጥ አልሸባብ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት 7 ሰዎች ሞቱ

65
ኢዜአ ሀምሌ 15/2011በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ ማለዳ ለተፈፀመው ጥቃት አሸባሪው ቡድን አልሸባብ ሃላፊነት ወስዷል። በከተማዋ የአውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኝ ሆቴል በር ላይ በተሽከርካሪ በተጠመደ ቦምብ በተፈፀመው ጥቃት 7 ሰዎች ሲሞቱ 27 ሰዎች እንደተጎዱም የህክምና ተቋማት ሃላፊዎች ተናግረዋል።
በከተማዋ ወደ ሚገኘው መዲና ሆስፒታል 7 አስክሬኖችን እና 27 ተጎጂዎችን ለምርምራና ለህክምና እንደተላኩ የተቋሙ ነርስ ኑራ ሀሰን ተናግረዋል። ከተጎጂዎቹ ውስጥ 17ቱ ህይወታቸው አስጊ ሁኔታ ውስጥ ነው ተብሏል። ምንጭ ፡-ሲጂቲኤን
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም