የፈረንሳይ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ጀምረዋል

107
ሀምሌ 15/2011 (ኢዜአ)የፈረንሳይ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሚኒስትር ብሩኖ ሊሜር ከአገሪቱ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሚኒስትር ኃላፊዎች ና ከተለያዩ ኩባንያዎች ተጠሪዎች ጋር ኢትዮጵያ ገብተዋል። ሚኒስትሩ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ጋር ኢትዮጵያና ፈረንሳይ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው  ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ከገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጋር የአገራቱን ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል። የብሩኖ ሊሜር ጉብኝት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፈው መጋቢት በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ተከትሎ የተዘጋጀ ነው። የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሚኒስትሩ የአንድ ቀን ጉብኝት ዓላማ በአገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከር እንደሆነ ተነግሯል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም