የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ታርጫ ካምፓስ ተማሪዎችን አስመረቀ

115
ሶዶ ኢዜአ ሐምሌ13/2011 የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዳውሮ ታርጫ ካምፓስ በልዩ ልዩ የሙያ መስክ ያሰለጠናቸውን ከ200 በላይ ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ። ተመራቂዎቹ የሰለጠኑት በሲቪል ኢንጂነሪግ፣ በማህበራዊ ሳይንስና በተፈጥሮ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በከፍተኛ ዲፕሎማ ደረጃ መሆኑን የካምፓሱ ዲን ዶክተር ሽመልስ አርጋው ገልጸዋል፡፡ ከተመራቂዎች መካከል 49 በመቶ ሴቶች ናቸው። የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፈሴር ታከለ ታደሰ በበኩላቸው የአካባቢው ማህበረሰብ የትምህርት ሥራው በአግባቡ እንዲሄድ ሠላምን በመጠበቅ ረገድ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ስራውን በምርምር በማስደገፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የዕለቱ የክቡር እንግዳ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር ዴኤታ ፕሮፌሴር አፈወርቅ ካሱ ባስተላለፉት መልዕክት ሁለንተናዊ ስብዕና የተሟላ ትውልድ ለማፍራት መንግሥት እየሰራ እንደሚገኝና በተለይም ተመራቂዎች ችግር ፈቺ ከመሆን አንጻር የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አሰስበዋል፡፡ “ዩኒቨርሲቲውም ከአካባቢው ማህበረሰብና መንግሥት ጋር በቅርበት በመስራት ያሉ ጸጋዎችን በመጠቀም የተክኖሎጂ ስርፀትን በማሳደግ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት ይገባዋል” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም