“ማህበራዊ ፍትህ ካልሰፈነ ሰላም ቅንጦት ነው” ሲሉ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ተናገሩ

105

ኢዜአ ሐምሌ 12/1011 የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ አስተዳደራቸው ኢ-ፍትሃዊነትንና ድህነትን በመዋጋት ድሆች ከሃገራቸው ሃብት ተቋዳሽ እንዲሆኑ እንሰራለን ሲሉ መናገራቸውን  ተገልጿል።

ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው ሁሉን አቀፍ ፍትህ ያለዘላቂ ሰላም ሊኖር እንደማችለው ሁሉ ማህበራዊ ፍትህም እንደዛው ያለ ሰላም ሊኖር አይችልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አሁንም ቢሆን በሃገሪቱ እኩልነት አለመስፍኑ በልማት ስራዎቻቸው ላይ አሉታዊ ጫና አሳድሮብናል ብለዋል።

ከፕሬዚዳንቱ ጀምሮ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ማለትም ከንግዱ ማህበረሰብ እስከ ጉልበት ሰራተኛው፣ ከህዝባዊ አካላት እስከ ሲቪክ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እስከ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድረስ  ኢኮኖሚያቸውን በማሳድግና በአስቸኳይ ድህነትን በመቀነስ መንግስታቸው ሁሉን አቀፍ መርሃ ግብር መቅረፁን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በማከልም ሰፋ ያለ ጥቁር ኢኮኖሚያዊ ሥልጣን ሰጭ ወይም ቢ-ቢቢኢኢን በሚገባ በመገንባት ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊያን፣ ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን በመርዳት እውነተኛና ቁሳዊ ስራዎች ላይ አፅንዖት  ሰጥተው እንደሚሰሩም ጭምር ማሳሰባቸው በዘገባው ተመልክቷል፡፡

መንግስት የደቡብ አፍሪካን ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ለማስተካከል ውጤታማ እንዳልሆነ ሲነገር የቆየ ቢሆንም ሰፋ ያለ ጥቁር ኢኮኖሚያዊ ሥልጣን ሰጭ ወይም የቢ-ቢቢኢኢን መዋቅርን መንግስት እንዲተው ግፊት ሲደረግበት መቆየቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ፕሬዝዳንት ራማፎሳም በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ኢ-ፍትሃዊ አሰራር ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውም  ተጠቁሟል፡፡

የደቡብ አፍሪካው ፓርላማ የመሬት አስተዳደር ሂደቱን ለማሻሻል የሚያስችሉ አዳዲስ ህግጋቶችን በማውጣት ሂደት ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አስታውሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም