በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራው የልኡካን ቡድን ባህርዳር ገባ

42
ባህር ዳር ኢዜአ ሀምሌ 12/2011በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራው የልኡካን ቡድን ዛሬ ባህር ዳር ከተማ ገባ። የልኡካን ቡድኑ እኩለ ቀን ባህርዳር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማሃኝ አስረስ ለኢዜአ እንደገለፁት የልኡካን ቡድኑ አባላት በቆይታቸውም ከአማራ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የጋራ ውይይት ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም በአካባቢው ያሉ የመስህብ ስፍራዎችን እንደሚጎበኙ እና ነገ በሚካሄደው የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የክብር እንግዳ ሆነው እንደሚታደሙ  ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም በአማራ ክልል በሚያካሄደው የርዕሰ መስተዳደር የሹመት ስነስርዓት ላይም ይታደማሉ ፡፡ አቶ ሙስጠፌ መሃመድ 100 የሚደርሱ የጎሳ መሪዎች፣ የኃይማኖት አባቶች ምሁራንና ሌሎች የማህበረተሰብ ክፍሎችን በመምራት ነው ባህር ዳር ከተማ የገቡት ፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም