አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም በአፍሪካ አህጉራዊ ውህደት እና ስራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ሊመክር ነው

145

ሀምሌ 12/2011 አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም በአፍሪካ አህጉራዊ ውህደት እና ስራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ሊመክር እንደሆነ አስታወቀ

በመርሃ ግብሩ መሰረት 28ኛው አለም አቅፍ የኢኮኖሚ ፎረም በመጭው መስከረም ወር አህጉራዊ ውህደት እና በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ውስጥ ያሉ ስራተኞችን መብት በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ውይይት በድቡብ አፍሪካ ሊካሄድ ነው ሲል ዥንዋ ዘግቧል።

እ.ኤ.አ ከመስከረም 4-6 2019 በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታዎን በሚካሄደው የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ዕድገት በማምጣት ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግም ይጠበቃል።

በተጨማሪም ይህ ፎረም በአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና የተቀናጀ እድገት እና ትብብር እንዲኖር በሚያደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ ሊወያይ እንደሚችል ዘገባው አትቷል።

አዲስ ፈጣሪ ትውልድ፣ አዲስ ግኝት ፈጠሪዎችን እና መሪዎችን በትክክል መገንባት መቻሏ አፍሪካ ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ እንዳስቻላት የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም አባሉ  ኤሊስ ካንዛ መናገራቸውን ዘገባው አስፍሯል።

ጥራት ያላቸው የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር እና በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ያሉ ስራተኞችን መብት በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እንዴት የጤና እንክብካቤን ማዘመን እና ወረርሽኝ መከላከል በሚቻልበት ዙሪያም ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በስብሰባው አፍሪካ  በተጋረጡባት ፈተናዎች ዙሪያ በመላው አለም ያሉ መንግስታት ፣ የንግድ እና የሲቪክ ማህበራት ይወያያሉ ተብሎ እንደምጠበቅ ዥንዋ ዘግቧል።