የታሸገ ውሃ የአንገት ላይ ሽፋን ተከለከለ

68
አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 18/2011 የመጠጥ ውሃ አምራች ድርጅቶች ይጠቀሙበት የነበረውን የውሃ የአንገት ላይ ሽፋን እንዳይጠቀሙ ተከለከሉ። የኢትዮጵያ የታሸገ ውሃና ለስላሳ መጠጥ አምራቾች ኢንዱስትሪ ማህበር አምራቾች፤ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች እና ሸማቾች ከሐምሌ 16 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ የታሸገ ውሃ አንገት ላይ ሽፋን እንዳያደርጉ፤ ህብረተሰቡም እንዳይጠቀም ብሏል። ማህበሩየውሃአምራችድርጅቶች፤የቦርዱአመራሮችናየሚመለከታቸውተቋማትበተገኙበትጋዜጣዊመግለጫሰጥቷል። የማህበሩ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጌትነት በላይ በጥናቶች እንደታየው የውሃ የአንገት ላይ ማሸጊያ አካባቢን ስለሚበክልና መልሶ መጠቀም ስለማይቻል ተከልክሏል። የአካባቢደንናአየርንብረትለውጥኮሚሽን ያደረገውጥናትእንደሚያሳየውይህየፕላስቲክሽፋንአካባቢንከሚበክሉቁሶችከዘጠኝእስከ 15 በመቶድርሻያለውናመልሶጥቅምላይምየማይውልነው። ከዚህ ባሻገር ከውጭ ለማስመጣት የውጭ ምንዛሪ የሚጠይቅና ጊዜ የሚወስድ በመሆኑም በአምራች ድርጅቶች ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር፤ አመሳስሎ ለመስራት የሚያጋልጥ ፤ አቧራን ከመከላከል ይልቅ አከማችቶ መያዙም ለመከልከሉ ምክንያቶች መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። የምግብ፣የመጠጥናየፋርማሲዩቲካልኢንዱስትሪልማትኢንስቲትዩትዋናዳይሬክተርአቶሰሎሞንታደለአምራችኢዱስትሪውበኢኮኖሚየደበረእንዲሆንየአካባቢውንደህንነትመሰረትአድርጎማምረት  እንዳለበትአሳስበዋል። የውሃ የአንገት ላይ ሽፋን ከውጭ አገር ለማስገባት አንድ ኩባንያ በዓመት ከ40 እስከ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያወጣል። በዚህ መሰረት በስራ ላይ ያሉት 85 የውሃ አምራች ኩባንያዎች ለዚሁ ተግባር ከ3 ነጥብ 5 እስከ 4 ሚሊዮን አሜሪካ ዶላር ያወጣሉ። የታሸገ ውሃ የአንገት ላይ ሽፋን ጥቅምም ሆነ በውሃው ይዘትና ጥራት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የሌለው መሆኑ 'የአንገት ላይ ሽፋን የሌላቸው የታሸጉ ውሃዎችን በማምረትና በመጠቀም አካባቢያን ፅዱና ውብ እናድርግ' በሚል መርህ በተሰጠው መግለጫ ላይ ተወስቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም