በአገር አቀፍ የፓራ ኦሎምፒክ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች ኦሮሚያ በሴቶች አማራ አሸነፉ

105
ሐምሌ 11/2011 የኢትዮጵያ የፓራ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ባለፉት አራት ቀናት ያካሄደው አገር አቀፍ ሻምፒዮና በወንዶች ኦሮሚያ በሴቶች የአማራ ክልል አሸናፊነት ተጠናቀቀ። በአገር አቀፉ የፓራ ኦሎምፒክ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአጠቃላይ ውጤት የአማራ ክልል አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። በኢትዮጵያ ፓራ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የውድድር ከፍል ኃላፊ አቶ ዮናስ ገብረማሪያም ውድድሩ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው የመላው አፍሪካ ፓራ ኦሊምፒክ ጨዋታ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚመረጡበት ነው ብለዋል። በውድድሩ በመካከለኛ ርቀት ጥሩ ሠዓት ያስመዘገቡ አትሌቶች መኖራቸው የታየበት እንደነበር ጠቁመዋል። ከውድድሩ በዊልቼርና በውርወራ ስፖርት ብዙ ስራ እንደሚጠይቅ መገዝብ ተችሏልም ብለዋል። በዚህ ውድድር ትግራይ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አልተካፈሉም። ክልሎቹ በአገሪቱ ከጸጥታ ጋር በተያያዘና ሌሎች ምክንያቶች መካፈል አለመቻላቸውን መግለጻቸውን ነው አቶ ዮናስ የተናገሩት። ውድድር ለመጀመረያ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይ ዓመታዊ ውድድር ለማድረግ እንደታሰበም ተገልጿል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም