የሮድ ቤልት ኢንሼቲቭ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ ዕድገት እንደሚያፋጥን ተገለፀ

63
ሐምሌ 11/2011 (ኢዜአ) ቻይና የቀረፀችው የሮድ ቤልት ኢንሼቲቭ የአፍሪካን ሁሉን አቅፍ እድገት እንደሚደግፍ ፓን አፍሪካ ባንከር  ገለጸ፡፡ በአፍሪካ የቻይና ትብብር ስታንዳርድ ባንክ ግሩፕ ኃላፊ ማንሻ አላጋቦሶ በናይሮቢ ለዣንዋ እንደተናገሩት የሮድ ቤልት ኢንሼቲቭ የመሰረተ ልማት አቅምን በማሳደግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተመሰረተ አለም አቀፍ ወኪል ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሀላፊው በናይሮቢ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ቻይና የወኪል መክፈቻ ስነ ስርዓት ወቅት እንደተናገሩት፤ የኤስያ፣ አፍሪካ እና አውሮፓ መንግሥታት በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም አካታች ልማትን ለማፋጠን የሮድ ቤልት ኢንሼቲቭን ዋነኛ መሳሪያ ነው ተብሏል። የሮድ ቤልት ኢንሼቲቭ አንዱ ምሳሌ የሆነው  የኬንያ የባቡር መስመር ዝርጋታ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ገፅታ እንደሚቀይረው ገልጸው፤ ይህ የኢንሼቲቭ አሰራር የአፍሪካ አገራትን አህጉራዊና ቀጠናዊ ውህደት ውስጥ ለሚያደርጉት ጅማሮ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ ነው መባሉ ሀላፊውን ጠቅሶ መረጃው አስታውሷል። ስታንዳርድ ባንክ ግሩፕ የአፍሪካን የፋይናስ ሴክተር እየመራ ያለ ድርጅት እንደሆነ ዥንዋ በድረ ገጹ አስፍሯል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም