የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ሰራተኞች 1 ሺህ 700 ችግኝ ተከሉ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ሰራተኞች 1 ሺህ 700 ችግኝ ተከሉ
89
አዲስ አበባ ሀምሌ 10/2011 ለአገር ልማት ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ወቅቱን ጠብቆ በመንከባከብ ለትውልድ አሻራን ማስቀመጥ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ገለጹ፡፡ የድርጅት ሰራተኞች በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ውስጥ 1 ሺህ 700 የዛፍ ችግኝ ተክለዋል። የድርጅቱየሥራኃላፊዎችናሠራተኞችችግኙንየተከሉትየጠቅላይሚኒስትርዶክተርአብይአህመድንአገራዊጥሪመሠረትበማድረግ 'የአረንጓዴ አሻራ' በሚልበተዘጋጀውየችግኝተከላመርሃግብርአማካኝነትነው። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ጉያ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ወቅቱን ጠብቆ መንከባከብና መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ በችግኝ ተከላው ላይ የተገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ችግኞቹ እንዲጸድቁ በመንከባከብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡ በተያዘው የክረምት ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ አራት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል፡፡ በመጪው ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ በመላው አገሪቱ 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ ቀርቧል። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።