ዩርሱላ ቮን ደ ለየን የመጀመሪያዋ ሴት የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሆኑ

77
ኢዜአ ሀምሌ 10/2011 የቀድሞዋ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ዩርሱላ ቮን ደ ለየን የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። የ60 ዓመቷ ዩርሱላ ቮን ደ ለየን የኮሚሽንን ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሰሩ የቆዩተን ዣን ክላውድ ዠንከርን ተክተው ይሰራሉ።
ባደረጉት ንግግርም “በእኔ ላይ ያሳያችሁት መተማመን በጠንካራዋና በተባበረችው አውሮፓ ላይ ያላችሁን መተማመን ያሳያል” ብለዋል። አዲሷ ፕሬዚዳንት በሚስጥር በተከናወነ የድምፅ አሰጣጥ አሸንፈው ነው ስልጣን የተቀዳጁት። አልጄዚራና ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም