በደቡብ ወሎ ተከስቶ የነበረውን የአንበጣ መንጋ ጉዳት ሳያደርስ ማስወገድ ተቻለ

47
ደሴ ኢዜአ ሐምሌ 9/2011 -በደቡብ ወሎ ዞን 8 ወረዳዎች ውስጥ ተከስቶ የነበረዉን የአንበጣ መንጋ ጉዳት ሳያደርስ ማስወገድ መቻሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ሰይድ ለኢዜአ እንደገለጹት ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በወረዳዎቹ  እስከ 40 የሚደርስ መንጋ ተከስቶ ነበር፡፡ የአንባጣው መንጋው ከተከሰተባቸው የዞኑ ወረዳዎች መካከል ቃሉ፣ አምባሰል፤ ደሴ ዙሪያ፣ ተሁደሬና አርጎባ የገኙበታል። የአንበጣመንጋውጉዳትሳያደርስማስወገድየተቻለው  በባህላዊመንገድብቻአርሶአደሩባደረገውርብርብእንደሆነአቶአሊአስረድተዋል። የአንበጣ መንጋው በአሸዋማና ሞቃት ጓሳ ላይ እንቁላል ለመጣል እየተዘጋጀ እንደነበር በባለሙያ በመረጋገጡ ቆርቆሮ፤ ሀይላንድና ሌሎችም አንበጣውን የሚረብሹ ከፍተኛ ድምጽ የሚያወጡ ቁሳቁሶች በመጠቀም እንዲባረር መደረጉን አመልክተዋል ። መንጋው የሚያርፍባቸው የመሸሸጊያ ስፍራዎችም እንዲጸዱ ተደርጓል። "ተወግዷል በሚል እሳቤ መዘናጋት እንዳይፈጠር ጥናትና አሰሳ እየተደረገ ነው" ያሉት አቶ አሊ አርሶ አደሩም በየጊዜው ማሳውን በመፈተሽ አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከት ለባለሙያ እንዲያሳውቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። የቃሉ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሐሽም ሙህዬ በሰጡት አስተያየት የአንበጣ መንጋው በግማሽ ሄክታር ማሳ በዘሩት በቆሎ ላይ ጉዳት ሳያደርስ መወገዱ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡ የጩኸት ድምጽ እንደማይወድ የተናገሩት አቶ ሐሽም አራት ቤተሰቦቻቸውን በማሰማራት ቆርቆሮና ሀይላንድ በማንኳኳት እንቁላል ሳይጥል ጥሎ እንዲሄድ ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ "በቀጣይነትም ሳንዘናጋ ማሳችንን በመከታተል ሰብላችንን ከጉዳት እንታደጋለን" ብለዋል፡፡ በደቡብ ወሎ ዞን በ2011/2012 የምርት ዘመን ለማልማት ከታቀደው  442 ሺህ ሄክታር መሬት ከ12 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት የሚጠበቅ ሲሆን እስካሁንም  ከ110 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ታርሶ በዘር መሸፈኑን ከዞኑ ግብርና መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም