ለውጡ ያስገኛቸውን ድሎች ለማስቀጠል እንደሚሰራ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ

78
ሀዋሳ ኢዜአ ሐምሌ 9/2011 በሀገር ደረጃ የተጀመረው ለውጥ ያስገኛቸው ተስፋ የሰነቁ ድሎች ቀጣይ እንዲሆኑ አባላቱንና መላው የክልሉን ህዝብ በማስተባበር የድርሻውን እንደሚወጣ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ። የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ ኮሚቴው ይህንን ያስታወቀው ለአስር ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው ባለስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ነው። የድርጅቱ ሙሉ መግለጫ ከዚህ በታች  የተመለከተው ነው ድርጅታችን ደኢህዴን ባለፉት28 ዓመታት የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን አስተባብሮ በመምራት በክልሉ ዉስጥ የልማት፤የሰላም፤የዴሞክራሲ ድሎችን አስመዝግቧል፡፡ በሀገራችን ከሚገኙ ብሔሮች ብሔረሰቦች 70 በመቶዉ ይዞ የተደራጀ ነዉ፡፡ የደቡብ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና፤ ህዝቦች ክልል ህዝቦችን በህብረ-ብሔራዊ አንድነት እየመራ የሚገኝ ዲሞክራሲያዊና ህዝባዊ ድርጅት ነው፡፡ ይህም ክልላችን የብዝሀነት ማዕከል፤ የአብሮነትና የአንድነት ማሳያ እንዲሆን አድርጓል፡፡ ደኢህዴንለህዝቦችእንድነትናለሀገርግንባታግንባርቀደምሚናዉንየተወጣናእየተወጣየሚገኝድርጅትሲሆንሀገራችንየገጠማትንተግዳሮቶችለመፍታትመፍትሄየሚሆኑዉሳኔዎችንያስተላለፈናስኬቶችንያስመዘገበድርጅትእንደሆነምገምግሟል፡፡በሀገራችንያጋጠሙችግሮችንለማለፍበተደረጉትግሎችከእህትድርጅቶችጋርበመሆንየራሱንጉልህሚናየተወጣድርጅትነዉ፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት በተደረጉ ትግሎች ሠላማዊ የስልጣን ሸግግር ለማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት ተወጥቷል፡፡ ስለሆነም ድርጅታችን ሀገራዊ ለዉጡ እዉን እንዲሆን ግንባር ቀደም ሚና የተወጣና ታሪካዊ ዉሳኔ ያስተላለፈ ድርጅት እንደመሆኑ ለቀጣይነቱም ግንባር ቀደም ሚናዉን እንዲወጣ ማዕካላዊ ኮሚቴዉ አጽንዖት ሰጥቷል፡፡ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ላለፉት 10 ተከታታይ ቀናት ባካሄደዉ ስብሰባ ሀገራዊ የስላምና ፀጥታ ሁኔታን ከአህጉራዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ገምግሟል፡፡ አሁን ሀገራችን ያለችበት ሁኔታም በዝርዝር አይቷል፡፡ ሁኔታዉን ለመቀየር ሁሉንም ህዝቦች በማረባረብ ሠላማችንን ማስከበር ከቻልን ግን ብሩህ ተስፋ እንዳለን በአፅንዖት አይቷል፡፡ የሠላምና የፀጥታ ሁኔታዉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ለመንግስት ብቻ የሚተዉ ሳይሆን የነቃ የህዝብ ተሳትፎ ጭምር የሚጠይቅ መሆኑን በመገንዘብ ድርጅቱ ህዝብን በማስተባበር የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን የሠላምና የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ለማድረግ ግንባር ቀደም ሆኖ እንደሚታገል አስምሮበታል፡፡ ዛሬም ዋነኛዉ ጠላት ድህነትና ኃላቀርነት መሆኑን የገመገመዉ ማዕከላዊ ኮሚቴዉ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር የሚደረገዉን ትግል የሚፈታተኑ ሁኔታዎች መግጠማቸዉን አይቷል፡፡ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ትኩረት ማነስ የስራ አጥነትና ድህነት የኑሮ ዉድነት የወጣቶችና የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዛሬም ያልተሻሻለ መሆኑን፡ ዘላቂ ሠላም የማረጋገጥና የህዝቦችን ደህንነት የማረጋገጥ ጉዳይ ትኩረት የሚሹ ተግባራት መሆናቸውን ገምግሟል፡፡ የክልላችንህዝቦችመንግስታዊአገልግሎትየማግኘትዕድሉንበሚመለከትየተለያዩየአደረጃጀትችግሮችበየደረጃውእየፈታመምጣቱንማዕከላዊኮሚቴውገምግሟል፡፡የክልልእንሁንጥያቄዎችንለመፍታትሳይንሳዊጥናትበምሁራንቡድንያስደረገውድርጅታችንበጥናቱግኝትላይምሰፊውይይትበማካሄድመግባባትፈጥሯል፡፡ ድርጅታችን የክልሉን ህዝቦች ጥያቄ በበቂ መረጃና ዕውቀት ላይ ተመስርቶ እና ህዝቡን ባሳተፈ መንገድ ለመመለስ ላለፉት ሰባት ወራት ባስጠናው ጥናት መሰረት ምላሽ ለመስጠት የተወያየ ሲሆን የሁሉንም ህዝቦች ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ውሳኔም አስተላልፏል፡፡ ጥናቱ ደረጃውን የጠበቀ አሳታፊ እና ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ በሚያግዝ አግባብ መመራቱንም አረጋግጧል፡፡ በጥናቱ ደኢህዴን የክልሉን ህዝብ መምራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተገኙ ትሩፋቶች፣ ተግዳሮቶች፣ መንስዔዎችና የመፍትሄ አማራጮች የያዘ ስለመሆኑ በጥልቀት በመፈተሸ ለቀጣይ የድርጅት የመሪነት ሚና እና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን በጥንካሬ ወስዷል፡፡ በመሆኑም በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም በክልሉ የሚነሱ ተጨማሪ ክልል ሆኖ የመደራጀት ጥያቄዎች ላይ ጊዜ ወስዶ በጥልቀት፤ ኃላፊነት በተሞላበትና በሰከነ ሁኔታ የመከረው የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የሚከተሉትን ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡ 1.ወቅታዊ ሀገራዊ የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ በእስካሁኑ ሂደት የታዩ አዎንታዊ ውጤቶችን የሚፈታተኑ ጉዳዮች መኖራቸውን የገመገመው ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅታችን ኢህአዴግ መሪነትና በህዝቦች ተሳትፎ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እንዳይቀለበስ ሁሉም አካላት በጋራ የኃላፊነት መንፈስ እንደሚገባቸው አስምሮበታል፡፡ በሀገርደረጃየተጀመረውየለውጥእንቅስቃሴተስፋየፈነጠቁጅምርውጤቶችየታዩበትሲሆንበጥንቃቄካልተያዘየሀገርንህልውናየሚፈታተኑናህዝባችንንስጋትውስጥሊያስገቡየሚችሉነባራዊናህሊናዊሁኔታዎችእየተስተዋሉመሆናቸውንተገንዝቧል፡፡ በቅርቡ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የሀገሪቱ የጦር መኮንኖች እስከ ህይወት ማጥፋት ድረስ የደረሰውን ጥቃት ድርጅታችን በፅኑ ያወግዛል፣ በፅኑም ይታገላል፡፡ 2.በእህትድርጅቶችመካከልከድርጅታዊዲስፕሊንውጪየሚወጡመግለጫዎችይህንንምተከትሎእየተደረሱያሉድምዳሜዎችከኢህአዴግመርህውጪመሆናቸውንበመገምገምየትኛውምዓይነትየሃሳብልዩነቶችንእንደወትሮውሁሉበድርጅቱባህልመሠረትማስተናገድእንደሚገባታይቷል፡፡ በሌላ መልኩ ደኢህዴን በውስጡ ያሉ ችግሮችን ታግሎ የሚያርምና የሚያጋጥሙ ችግሮችና ፈተናዎችን ከህዝቡ ጋር በመሆን የመፍታት ባህልና ልምድ ያለው ድርጅት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ እኔ አውቅልሃለሁ በሚመስል መንገድ ከሩቅ የሚሰነዘሩ ሂደቱን ያልተከተለ አመራር የማይቀበል መሆኑን ማዕከላዊ ኮሚቴው ያስገነዝባል፡፡ 3.ክልላዊወቅታዊፖለቲካናፀጥታሁኔታልዩትኩረትየሚሻመሆኑንማዕከላዊኮሚቴውበዝርዝርገምግሟል፡፡ሀገራዊፖለቲካእናፀጥታድባብተከትሎበክልሉውስጥየሚታዩአዝማሚያዎችየህግየበላይነትአደጋውስጥየመግባትየኢ-መደበኛአደረጃጀቶችእንቅስቃሴዎችስርአትመያዝያለባቸውመሆኑንተሰምሮበታል፡፡ በዚህ ሂደት ለታዩ ጉድለቶች ሀገራዊ ሁኔታ የራሱ አሉታዊ አስተዋዕፆ ያለው ቢሆንም ዋናው ችግር የድርጅታችን ውስጣዊ ሁኔታ መሆኑን ማዕከላዊ ኮሚቴው በጥልቀት ተወያይቷል፡፡ ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ በየደረጃው ያለው አመራር ድርሻ ሰፊ መሆኑም ታይቷል፡፡ ስለሆነም እንደ ሀገር እና እንደ ክልል ከገባንበት ያለመረጋጋት ለመውጣት የድርጅቱ ውስጣዊ ጥንካሬ ወሳኝ መሆኑን የድርጅቱ አመራሮች በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ እና ህዝባዊ ውግንና መንቀሳቀስ የሚጠይቀን ወቅት ላይ መሆናችንን መተማመን ላይ ተደርሷል፡፡ በመብት ጥያቄ ሽፋን የሚደረጉ የትኛውንም ኢ-መደበኛ እንቅስቃሴዎችን ስርዓት ለማስያዝ እንዲሁም የህዝቦችን ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ማስከበር ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን ማዕከላዊ ኮሚቴው ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ 4.በክልል የመደራጀት ጥያቄን በተመለከተ የህዝቦች ህገ-መንግስታዊ መብት መሆኑን ድርጅታችን ይገነዘባል፡፡ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ሲነሳ የነበረው ከአንድ አካባቢ ብቻ ባይሆንም ጥያቄውን በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ድርጅቱ በአስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በወሰደው አቋም መሰረት በዝርዝር ህዝቡን ያሳተፈ ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በጥናቱ የቀረቡ አማራጮችን በጥልቀት በመመርመር፣ የህዝቡን የጋራ ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጠውን አማራጭ በመውሰድ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች በሚመለሱበት አግባብ ላይ አቋም ተወስዷል፡፡ በክልላችን መላው ህዝብ ምክክርና ውይይት የሚያደርግበት ሆኖ በአንድ በኩል በጥናቱም የተገኘውን የክልሉ ህዝቦች አብሮ የመቀጠል ፍላጎትን ባከበረ በሌላ ጎኑ ደግሞ ጉባኤውን ውሳኔ ተግባራዊ ባደረገ መንገድ እና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ የመምራት ኃላፊነት ለመወጣት ማዕከላዊ ኮሚቴው ተስማምቷል፡፡ 5. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በህብረ-ብሔራዊነት ላይ እየተገነባ ያለው የፌዴራል ሥርዓት ትሩፋቶችን ያስመዘገበ ሲሆን በሂደቱ የታዩ ተግዳሮቶች በማረም ሀገራችን በደረሰችበት የዕድገት ደረጃ በማሻሻል ለፌዴራል ሥርዓቱ ይበልጥ መጎልበትና ቀጣይነት የምንታገል መሆኑን አቋም ተወስዷል፡፡ ከሁሉ በላይ ህበረ-ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ለማጎልበት ማዕከላዊ ኮሚቴው አጽንኦት ሰጥቷል፡፡ 6.በእያንዳንዱአከባቢያለውንየልማትሁኔታበተመለከተበድርጅታችንመሪነትበክልላችንየተመዘገቡየልማትውጤቶችእንደተጠበቁሆነውበተለያየመልኩየሚገለጽፍትሃዊተጠቃሚነትየመልካምአስተዳደርእናየአመራርሥርዓታችንላይየሚታዩችግሮችመፈታትእንዳለባቸውተወስዷል፡፡ ከዚህም በመነሳት በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ በክልሉ ያሉ ህዝቦች በጋራ መልማት እንዳለብን በመግባባት ህዝቡን ባሳተፈ ሁኔታ የክልሉን ህገ-መንግስት ከማሻሻል ጀምሮ ሌሎች ዝርዝር የህግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁ አቋም ተወስዷል፡፡ ውድ የድርጅታችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፣ ድርጅታችን ደኢህዴን ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ ያበረከታችሁት ድርጅታዊ አስተዋጽኦ ከገባንበት ፈተና ለመውጣት ያስቻለ ሆኗል፡፡ የድርጅት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ አቋም የተወሰደበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ ስለሆነም የተጀመረው ድርጅታዊ ሪፎርም በማጠናከር እንደወትሮ ሁሉ ግንባር ቀደምትነት ሚናችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የተከበራችሁየክልላችንህዝቦች፣በተለያዬመልኩየሚገለጽየልማት፣የመልካምአስተዳደርእናየአደረጃጀትጥያቄዎችውስጥምሆናችሁምላሽእንዲሰጣችሁላሳያችሁትትዕግስትድርጅቱምስጋናያቀርባል፡፡ይህትዕግስታችሁበመሪድርጅቱእናበመንግስትላይእምነትበመጣልየሚታዩችግሮችበጋራቆመንእንድንፈታየበኩላችሁንአስተዋጽኦእንዳበረከታችሁያሳየንነው፡፡ችግሮችንበውይይትናበምክክርየመፍታትአማራጭብቻበመከተልዛሬለደረስንበትደረጃያበረከታችሁትአስተዋጽኦታሪክየሚረሳውአይደለም፡፡ዛሬምድርጅታችንበጽኑመስመርላይበጽናትበመቆምየሚያጋጥሙትንፈተናዎችበድልለመወጣትያለውንዝግጁነትያረጋግጣል፡፡ስለሆነም በድርጅቱ ላይ ያላችሁን እምነት በማጎልበት ለውጡን ከዳር ለማድረስ የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የተከበራችሁየክልላችንአርሶእናአርብቶአደሮች፣የክልላችንህዝብአብዛኛውንቁጥርበመያዛችሁብቻሳይሆንባለፉትዓመታትለተመዘገበውየኢኮኖሚዕድገት፣ለህዝቦችፍትሃዊተጠቃሚነትእናለድርጅታችንቀጣይነትዋልታናማገርመሆናችሁንነጋሪአያሻውም፡፡ ያገኛችሁትን ትሩፋቶች ጠብቃችሁ በቀጣይ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መዋቅራዊ ችግሮች እንዳሉ ተገንዝበናል፡፡ በመሆኑም ከድህነት ለመላቀቅና ለተሻለ ህይወት የምታደርጉትን ጥረት ከጎናችሁ በመቆም አለኝታነታችንን ለማረጋገጥ ዛሬም የፀና እምነት እንዳለን እናረጋግጣለን፡፡ የተከበራችሁየክልላችንወጣቶች፣በክልሉበሁሉምአካባቢዎችየወጣቶችተሳትፎናየኢኮኖሚተጠቃሚነትጥያቄአንገብጋቢናየተለየምላሽመስጠትየሚጠይቅመሆኑንበጥልቀትያየውማዕከላዊኮሚቴውበቀጣይየክልሉየልማትኮሪደሮችንለይቶየጋራሀብቶችንበማልማት፣ወጣቱንተጠቃሚነትለማረጋገጥየሚሰራመሆኑንአቅጣጫአስቀምጧል፡፡ በመሆኑም በክልላችን ያለውን የጋራ ፀጋ መሰረት ያደረጉ አዳዲስ የልማት ቀጠናዎችን በመፍጠር የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ቆርጠን መነሳታችንን እንገልጻለን፡፡ ስለሆነም የክልላችን ወጣቶች ከድርጅታችን ጎን በመሰለፍ የማይተካ አዎንታዊ ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የተከበራችሁ የክልላችን ሴቶች እስካሁን ለተገኙ ትሩፋቶች ሚናችሁ የላቀ ሲሆን ባጋጠመን ተግዳሮቶች ቀዳሚ ተጎጂ መሆናችሁ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የሴቶችን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማስፋት በእስካሁኑ ጉዟችን የነበሩ ጉድለቶችንም ለማረም ከምንም ጊዜ በላይ ዝግጁነታችንን እናረጋግጣለን፡፡ የክልላችን ሴቶች ከህብረተሰቡ ውስጥ ከቤተሰብ ጀምሮ ያላችሁን ግዙፍ ሚናችሁን ይዛችሁ ከድርጅታችን ጎን ሆናችሁ ትግላችሁን እንድታጠናክሩ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የተከበራችሁ የክልላችን ምሁራን ድርጅታችን ባስመዘገበው ስኬቶች ለነበራችሁ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ክብር አለን፡፡ አሁንም ከሰፊው የዕውቀት ማዕድ ካገኛችሁት ልምድና የህብረተሰብ ችግሮች ላይ መፍትሄ ለመስጠት ያላችሁ የመተንተን አቅማችሁን ሳትነፍጉ ለሀገራችሁና ለህዝባችሁ ለወገናችሁ ለማበርከት ከጎናችን እንድትሰለፉ ጥሪ ያቀርባል፡፡ ውድ የሀገራችን ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ በክልላችን ብሎም በሀገራችን ለተመዘገበው ልማት የጀርባ አጥንት በመሆን ለምታበረክቱት ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በክልላችን ያለውን የመልማት ጸጋ በጋራ ለማልማትና ህዝባችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከምንግዜውም በላይ ተዘጋጅተናል፡፡ ስለሆነም በግልና በጋራ ሆናችሁ አብረን ለመስራት ጥሪ ያቀርባል፡፡ ውድ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የክልላችን ህዝቦች መለያና መታወቂያ የሆነውና እየተገነባ የመጣውን ደቡባዊ ስነ ልቦና ለክልላችን ህዝቦችም ሆነ ለሀገር ግንባታ ያለው ፋይዳ ትርጉም ያለው ነው፡፡ ይሁንን እምቅ አቅም ይበልጥ በማውጣት ረገድ ኪነ ጥበብ ያለው ሃይል ላቅ ያለ በመሆኑ የህዝቦችን ትስስርና አንድነት በቀጣይነት ለመገንባት እንድታውሉ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የተከበራችሁ እሀት ደርጅቶችና አጋሮች ደኢህዴን/ኢህአዴግ የክልሉን ህዝቦች ሰላም ልማት ዴሞክራሲ ብሎም ለሀገራዊ አንድነትና ክብር የበኩሉን አዎንታዊ ሚና ሲጫወት የቆየ ድርጅት ነው፡፡ በሀገር ግንባታ ሂደት የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደመጣ ሁሉ ዛሬም ለሀገራችንና ለህዝቦቿ እንዲሁም ለዜጎቿ ክብር መብት ነፃነት ብልጽግና ዴሞክራሲያዊ አንድነት ተግቶ ይታገላል፡፡በዚህ ሂደት ከጎናችን እንደቆማችሁ ሁሉ ዛሬም የተለመደው አዎንታዊ ሚናችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባል፡፡ የተከበራችሁተፎካካሪፓርቲዎችበተለያየሙያውስጥያላችሁበሙሉደኢህዴንየእስካሁንስኬቶቹንጠብቆማቆየትሳይሆንያጋጠሙትንተግዳሮቶችበመወጣትለሀገራችንመፃኢተስፋአዎንታዊሚናለመጫወትቆርጦተነስቷል፡፡ይህሂደትየሁላችሁምአዎንታዊድጋፍናእይታይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በድርጅታችን የሚቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች መመዘን ያለባቸው ከህዝቡ ሰላምና የህግ የበላይነት ዘላቂ ጥቅም አንጻር መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ገንቢ ሚናችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም