የጨፌ ኦሮሚያ 10ኛ መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የጨፌ ኦሮሚያ 10ኛ መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ
55
አዳማ ሐምሌ 9 /2011 የጨፌ ኦሮሚያ አራተኛ ዓመት አምስተኛ የሰራ ዘመን አስረኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ። ጨፌው አስር የክልሉ የስራ አስፈፃሚ አካላትና አስራ ሶስት የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። በተመሳሳይ የኦሮሚያ ብሮድ ካስቲንግ ኔት ወርክ ዋና ዳይሬክተርና የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ በማድረግ አቶ ዝናቡ አስራትና ዶክተር ቶላ በሪሳ በቅደም ተከተል ሹመታቸውን አፅድቋል። በሌላ በኩል የጨፌ አባላት አሰራርና የስራ ምግባር ደንብ ለማሻሻል የቀረበውን አዋጅ መርምሮ አፅድቋል። የጨፌ ኦሮሚያ አስረኛ መደበኛ ጉባኤ በሶስት ቀናት ቆይታው የቀረበለትን አስራ ሶስት የተለያዩ አጀንዳዋችን መርምሮ በማፅደቅ ዛሬ ተጠናቋል።