ቱርክ ከሩሲያ ጋር በጥምረት ኤስ-400 የሚሳኤል መቃወሚያዎችን ለማምረት አስባለች-ኤርዶሃን

121
ሐምሌ 9/2011 የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ሀገራቸው ከሩሲያ የገዛቻቸው የኤስ-400 የሚሳኤል መቃወሚያዎችን በመጪው የፈረንጆቹ 2020 ሚያዚያ ሙሉ ለሙሉ እንደምትረከብ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት በቀጣይ ኤስ-400 መሳሪያዎችን አንካራ ከሞስኮ ጋር በጥምረት ለማምረት ማሰቧን ነው ያነሱት። “ኤስ-400 መሳሪያ ሀገራችንን ማጥቃት የሚፈልጉ ሃይሎችን ኢላማ ለመከላከል የሚያስችል ነው” ሲሉ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከሸፈ የተባለበትን ሶስተኛ ዓመት ለማክበር ለተበሰበሰው ህዝብ ተናግረዋል። አንካራ ከሩሲያ የሚሳኤል መቃወሚያዎችን ማስገባቷን ተከትሎ ከዋሽንግተን በኩል ማዕቀብን ጨምሮ ቅጣት ይጠብቃታል እየተባለ ነው። የቱርክ መሪ ጣይብ ኤርዶሃን ቀደም ብለው “አሜሪካና ቱርክ ስትራቴጂያዊ አጋር በመሆቸው ማዕቀብ ይጫንብናል ብለን አናስብም” ብለው እንደነበር አልጄዚራ ዘግቧል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም