ኢራፓ እና ኢዜማ ተዋሃዱ

122
አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 8/2011 የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ /ኢራፓ/ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ/ ተዋሃዱ። የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ኢራፓ/ የሚለው መጠሪያው ከስሞ ከኢትዮጵያ ዜጎች ለፍትህ ፓርቲ ጋር ውህደት መፍጠሩን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ኢዜማ ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም በይፋ ሲቋቋም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን በድርጅት መሪነት፣ አቶ አንዷለም አራጌን በምክትልነት፣ እንዲሁም አቶ የሺዋስ አሰፋን የፓርቲው ሊቀመንበር ፣ ዶክተር ጫኔ ከበደን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድረጎ መሰየሙ ይታወሳል። ፓርቲው ያልተማከለ አስተዳደር (ፌዴራላዊ) ሥርዓትን መከተለን ምርጫው ያደረገ ሲሆን ከፍተኛው የመንግሥት ሃላፊነት በሕዝብ ቀጥታ ምርጫ በሚመረጥ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት ይከተላል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም