ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ 3ኛውን አገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ማለዳ ላይ አከናውነዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ 3ኛውን አገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ማለዳ ላይ አከናውነዋል
91
አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 7/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሶስተኛውን አገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ መሰረት በማድረግ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ የፅዳት ስራ አካሂደዋል። በፅዳት ዘመቻው የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳም ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከአቶ ሽመልስ ጋር በመሆን የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር ፅህፈት ቤት ቅጥር ግቢንም አፅድተዋል። ከፅዳት ስራው በኋላም በፅህፈት ቤቱ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል። ዛሬ በተካሄደው ሶስተኛው አገር አቀፍ የፅዳት መርሃ ግብር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባለፈው ወር በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝተው የፅዳትና የችግኝ ተከላ ማከናወናቸው ይታወቃል።