ህንድ በአስር ዓመት ውስጥ 271 ሚሊዮን ዜጎችዋን ከድህነት አረንቋ አስወጥታለች

113
ኢዜአ ሀምሌ 5/2011 የተባበሩት መንግስታት ድርጅትየ2019 ዘርፈ ብዙ ድህነትን አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው ህንድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2005-2006 እስከ 2015-2016 ባለው ግዜ 271 ሚሊዮን ህንዳውያን ከድህነት አረንቋ ወጥተዋል፡፡ ይህ ውጤትም ህንድ ድህነትን በከፍተኛ ፍጥነት በመቀነስ ቀዳሚ ሀገር አድርጓታል፡፡
የድህነት ቅነሳ መስፈርቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው ሃብት ማፍራት ፣ የምግብ አቅርቦት የንጽህና እና የአመጋገብ ስርዓትን ያካተቱ አስር መስፈርቶችን ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም 8 ነጥብ 8 ከመቶ የህንድ ህዝብ በከባድ ዘርፈ ብዙ ድህነት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን 19 ነጥብ 3 ከመቶ ህዝብዋ ለድህነት ተጋላጭ ነው ተብሏል፡፡ በሌላ መልኩ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን የዓለማችን ህዝብ ዘርፈ ብዙ ድህነት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ ሪፖርቱ በአገራት መካከል ሰፊ የእኩልነት ልዩነት እንዳለም ያመለክታል ፡፡ ከአጠቃላይ የድህነት መጠኑ ከሳህራ በታች እና ደቡብ ኤስያ የሚገኙ አገራት 84.5 ከመቶ ድርሻ በመያዝ ቀዳሚ ናቸው፡፡ የዓለማችን ድሃ ተብሎ ከተለዩት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ህዝብ ከግማሽ በላይ ማለትም 663 ሚሊዮኑ ከ18 ዕድሜ በታች የሆኑት ህጻናት ናቸው ተብሏል፡፡ የመረጃው ምንጭ ዥንዋ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም